Kishore Kumar Hits

Dawit Mellesse - Ye-Mishit Kokeb lyrics

Artist: Dawit Mellesse

album: Lottery


አንቺ የምሽት ኮከብ ጨረቃ
ድንገት በህልሜ አይቼሽ ብነቃ
እንዳበባ ፈክተሽ ታየሽኝ
እስኪ አንዳፍታ ብቅ በይልኝ
አንቺ የምሽት ኮከብ ጨረቃ
ድንገት በህልሜ አይቼሽ ብነቃ
እንዳበባ ፈክተሽ ታየሽኝ
እስኪ አንዳፍታ ብቅ በይልኝ
መስኮት ከፍቼ ውጭ ባይሽ
ጨረቃም የለች አንችም ጠፋሽ
ዳግም አልተኛ ምን አደርጋለሁ
እስክትመጪ እጠብቃለሁ
ሌሊት እየመጣሽ ሰው በሌለበት
እንቅልፍ አጣሁኝ እንዳልተኛበት
ከቤቴ መተሽ በቁም ነገር
አንዴ አነጋግሪኝ ስለፍቅር
የቁም ቅዠት ነው ወይስ ደሞ ያመኛል
ብቻዬን ሆኜ የማወራሽ ይመስለኛል
ናፍቆቴን እንኪ ናፍቆትሽን ስጭኝ
መቼም አንችው ነሽ ውስጤን የምታውቂልኝ
ነፍሴ ነፍሴ ነፍሴ አንቺ እኮ ነሽ
ታድያ ለምን ለምን ትሸሺያለሽ
ማታ ማታ ነይ ነይ ማታ ማታ
ቀን ቀን ብቻ አይበቃም ጨዋታ
አንቺ የምሽት ኮከብ ጨረቃ
ድንገት በህልሜ አይቼሽ ብነቃ
እንዳበባ ፈክተሽ ታየሽኝ
እስኪ አንዳፍታ ብቅ በይልኝ
አንቺ የምሽት ኮከብ ጨረቃ
ድንገት በህልሜ አይቼሽ ብነቃ
እንዳበባ ፈክተሽ ታየሽኝ
እስኪ አንዳፍታ ብቅ በይልኝ
በህልሜ መተሽ አታስጨንቂኝ
እቀፊኝ እና ውስጤን አሙቂኝ
ፍቅርን በጉያሽ አትደብቂው
ግለጭው እና እኔም ልሙቀው
እስኪ ንገሪኝ የመምጫሽን
ትዘገያለሽ ወይስ አሁን
አንቺን ስጠብቅ ስራም አልሰራ
መገናኛውን ቁርጡን አደራ
አንቺ የኔ ጉብል አንቺ የኔ ዘንጋታ
ሁለመናሽን እንድጠግበው ዛሬ ማታ
የልባችን እንጫወት ጨዋታ
ከተገናኘን እንቅልፍም የለ መኝታ
ምስጢራችንን እንጨዋዎት
ናፍቆት ወቶልኝ ሰውነቴም ይደሰት
ከደጃፍ ቆሜ እጠብቃለሁኝ
ፍቅርሽን ይዘሽ ቶሎ ግቢልኝ
የቁም ቅዠት ነው ወይስ ደሞ ያመኛል
ብቻዬን ሆኜ የማወራሽ ይመስለኛል
ናፍቆቴን እንኪ ናፍቆትሽን ስጭኝ
መቼም አንችው ነሽ ውስጤን የምታውቂልኝ
አንቺ የኔ ጉብል አንቺ የኔ ዘንጋታ
ሁለመናሽን እንድጠግበው ዛሬ ማታ
የልባችን እንጫወት ጨዋታ
ከተገናኘን እንቅልፍም የለ መኝታ
ምስጢራችንን እንጨዋዎት
ናፍቆት ወቶልኝ ሰውነቴም ይደሰት
ከደጃፍ ቆሜ እጠብቃለሁኝ
ፍቅርሽን ይዘሽ ቶሎ ግቢልኝ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists