Kishore Kumar Hits

Dawit Mellesse - Atemekibet lyrics

Artist: Dawit Mellesse

album: Lottery


የኔ ውብ አበባ ነሽ
ፅጌሬዳ ትኩስ የፈነዳ
ልቤም አንቺን ብሏል
ተቀበይው ያዢው እንዳይጎዳ
ይሄ ውብ አበባሽ
ፅጌሬዳ መሳይ ያ ቁመናሽ
ጊዜውን ጠብቆ
ረጋፊ ነው ያ ውብ ገላሽ
በምን ዘዴ ላስረዳሽ የፍቅርን ትርጉም
ሁሉም ተኖ ያልፋል እንደጉም
በለጋ እድሜሽ ካሁኑ እስኪ አስቢበት
ኋላ እንዳይቆጭሽ እወቂበት
እሸትም ሲበላ በወቅቱ
በጊዜው ሲሆን ነው ውበቱ
አንዴ ካመለጠ ሰዐቱ
ምን ሊጠቅም ኋላ ቁጭቱ
በቁንጅናሽ ብማረክም ብታጪም አቻ
ቁም ነገር አጣሁብሽ ውበትሽን ብቻ
ውበት ብቻውን ሲሆን የለውም ዋጋ
ቁም ነገር እንጂ ለሰው ሀብትና ፀጋ
የኔ ውብ አበባ ነሽ
ፅጌሬዳ ትኩስ የፈነዳ
ልቤም አንቺን ብሏል
ተቀበይው ያዢው እንዳይጎዳ
ይሄ ውብ አበባሽ
ፅጌሬዳ መሳይ ያ ቁመናሽ
ጊዜውን ጠብቆ
ረጋፊ ነው ያ ውብ ገላሽ
በህይወትሽ ቀልደሽ የማታ የማታ
ተይ ትወድቂያለሽ የማይሆን ቦታ
ህፃን ብዬ ለሰው አላስመክርሽ
ኑሮ እና ጊዜ ያስተምርሽ
በአይንሽ ፍላፃ ተመትቶ
የወደቀው ልቤ ተረትቶ
የፍቅርሽን ውሃ ተጠምቶ
ለመኖር አልቻለም ረግቶ
ባንቺው ታውሮልሽ አይኔ ታውሮ
ስሜቴን ተረጂልኝ የኔንም ኑሮ
በግል ብቻ ሲሆን የለውም ፋይዳ
አብረሽኝ እንያዘው እንዳልጎዳ
ተይ አትኩራሪ በውበተሽ
ተይ አትመኪ በቁንጅናሽ
ገላ አፈር ነው እወቂበት
ጊዜ ሳያልፍበት
በቁንጅናሽ ብማረክም ብታጪም አቻ
ቁም ነገር አጣሁብሽ ውበትሽን ብቻ
ውበት ብቻውን ሲሆን የለውም ዋጋ
ቁም ነገር እንጂ ለሰው ሀብትና ፀጋ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists