Kishore Kumar Hits

Shewandagne Hailu - Skalegne lyrics

Artist: Shewandagne Hailu

album: Skalegne


ባካል ተራርቀን ናፍቄሽ ናፍቀሺኝ
ነገረኝ ስቅታ ዛሬ እንዳነሳሺኝ
ከሆነም ሌላ ሰው ክፉ የሚያወራ
ስቅታዬ ሳይብስ ስሙን ቶሎ ልጥራ
ስቅ አለኝ ማን አነሳኝ ደሞ
ስቅ አለኝ ማን አነሳኝ
ስቅ አለኝ ማን አነሳኝ ደሞ
ስቅ አለኝ ማን አነሳኝ
እድሌ ነው መሰል ሰው ርቆም አይረሳኝ
በክፉ ነው በደግ በምን ደሞ አነሳኝ
ስሜ ባክኖ እንዳይሆን በሰው ምላስ ታሞ
ስቅ ይለኛል ዛሬ ማን አነሳኝ ደሞ
ስቅ አለኝ ማን አነሳኝ ደሞ
ስቅ አለኝ ማን አነሳኝ
ስቅ አለኝ ማን አነሳኝ ደሞ
ስቅ አለኝ ማን አነሳኝ
ያራቀው ጎዳና ወስዶ እስኪመልሰው
በደግ ያነሱታል የሚወዱትን ሰው
ዛሬም ያለወትሮው ስቅ ይለኛል ምነው
ስሜ አንቺ ጋር ካለ ይሁን ለበጎ ነው
ስቅ አለኝ ማን አነሳኝ ደሞ
ስቅ አለኝ ማን አነሳኝ
ስቅ አለኝ ማን አነሳኝ ደሞ
ስቅ አለኝ ማን አነሳኝ
ማን አነሳኝ ደሞ
ስሜ አንቺጋ ካለ ይሁን ለበጎ ነው
ስቅ አልኩኝ ደግሜ ደግሜ
የት ዋለብኝ ይሁን ስሜ
ርቆም ማይረሳኝ አፍሽ
በምን ትዝ አልኩሽ (ስቅ አለኝ)
ስቅ አልኩኝ ደግሜ ደግሜ
ማንጋ ይሆን ስሜ (ስቅ አለኝ)
ርቆም ማይረሳኝ አፍሽ
በምን ትዝ አልኩሽ (ስቅ አለኝ)
ስቅ አልኩኝ ደግሜ ደግሜ
ማንጋ ይሆን ስሜ (ስቅ አለኝ)
ስቅ አለኝ ማን አነሳኝ ደሞ
ስቅ አለኝ ማን አነሳኝ
ስቅ አለኝ ማን አነሳኝ ደሞ
ስቅ አለኝ ማን አነሳኝ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists