Kishore Kumar Hits

Shewandagne Hailu - Ande Leben lyrics

Artist: Shewandagne Hailu

album: Sitotash


በቀረብኩሽ ቁጥር ለምጄሽ
ለምጄሽ ጉድ ሳልሆን ወድጄሽ
ባገኘሁሽ ቁጥር አፍቅሬሽ
አፍቅሬሽ ካልሆንኩኝ አብሬሽ
ገና ይህን ሳስብ ገና
ፈራሁ ፍቅርን እንደገና
ገና ይህን ሳስብ ገና
ፈራሁ መዉደድ እንደገና
የልቤ ስጋት ዛሬስ መች አለቀና
እንዴት ያሁኑን ልመን ያምናዉ ሳይቀና
ያኔ ማፍቀሬ ከቶኝ ከማያልቅ እዳዉ
መጭዉ ደስታዬ ሆኖ ዉስጤን ላይረዳዉ
እንዴት ዳግም ወድጄ ራሴን ልጉዳዉ
እስኪ ልቤ ረጋ በል እስኪ ልቤ
ዳግም ማዘን አልሻም ሰዉ ቀርቤ
እስኪ ልቤ ረጋ በል እስኪ ልቤ
ይሻለኛል መኖሩ ተሰብስቤ
አንድ ልቤን ሰጥቸሽ ካንድ ልቤ
ካንቺ ጋራ ባልኖርስ እንዳሳቤ
አንድ ልቤን ብሰጥሽ በርግጠኛ
ያንችስ ምላሽ ምን ይሆን ንገሪኛ
በቀረብኩሽ ቁጥር ለምጄሽ
ለምጄሽ ጉድ ሳልሆን ወድጄሽ
ባገኘሁሽ ቁጥር አፍቅሬሽ
አፍቅሬሽ ካልሆንኩኝ አብሬሽ
ገና ይህን ሳስብ ገና
ፈራሁ ፍቅርን እንደገና
ገና ይህን ሳስብ ገና
ፈራሁ መዉደድ እንደገና
በፊት ቸኩሎ ልቤ ስልተቀጣ
ዛሬም ወዳንቺ አሮጠም እዳ ሊያመጣ
ትንሽ ረጋ ማለት ለኔ ይጠቅመኛል
ዉበት አይቼ ከላይ ምን ያፈጥነኛል
ለኔ ብሎት የመጣስ የት ያመልጠኛል?
እስኪ ልቤ ረጋበል እስኪ ልቤ
ዳግም ማዘን አልሻም ሰዉ ቀርቤ
እስኪ ልቤ ረጋ በል እስኪ ልቤ
ይሻለኛል መኖሩ ተሰብስቤ
አንድ ልቤን ሰጥቸሽ ካንድ ልቤ
ካንች ጋራ ባልኖርስ እንዳሳቤ
አንድ ልቤን ብሰጥሽ በርግጠኛ
ያንችስ ምላሽ ምን ይሆን ንገሪኛ
አንድ ልቤን ሰጥቸሽ ካንድ ልቤ
ካንች ጋራ ባልኖርስ እንዳሳቤ
አንድ ልቤን ብሰጥሽ በርግጠኛ
ያንችስ ምላሽ ምን ይሆን ንገሪኛ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists