አዝኖ ልቤ ሆኖ ስደተኛ በሰው ሀገር
ከሚከፋው በባይተዋር ኑሮ ከሚቸገር
ሸገር ላይ አዲስአበባ
ከትውልዴ ቤት ሀገሬ ልግባ
ሸገር ላይ አዲስአበባ
ከትውልዴ ቤት ሀገሬ ልግባ
አዝኖ ልቤ ሆኖ ስደተኛ በሰው ሀገር
ከሚከፋው በባይተዋር ኑሮ ከሚቸገር
ሸገር ላይ አዲስአበባ
ከትውልዴ ቤት ሀገሬ ልግባ
ሸገር ላይ አዲስአበባ
ከትውልዴ ቤት ሀገሬ ልግባ
አልተመቸኝም በሰው ሀገር አውሎኝ እድል ካለቦታው
መንገደኛ ነኝ የህልም አለም ነገ ዛሬ የምል ሳመነታ
ቀን ይጠብቃል እንጂ ጊዜ ማንስ ይቀራል ከሀገር ወቶ
ምኞት እንደሆን ማብቂያም የለው
በአንዱ ይፈሳል በአንዱ ሞልቶ
ቤቴ ሀገሬ አዲስአበባ
ካንቺ እረቄ ስንት አደይ ገባ
በእግሬ ብዞር ብውል ፍለጋ
ለካ አዳሬ ካንቺ ነው ለካ
ለካ አዳሬ... ለካ አዳሬ
ነበር ሀገሬ... ለካ አዳሬ
ከእናት ፍቅሬ... ለካ አዳሬ
በል ምራኝ እግሬ... ለካ አዳሬ
ከአባቴ ሀገር... ለካ አዳሬ
ውሰደኝ ሸገር... ለካ አዳሬ
ከእናት ምድሬ... ለካ አዳሬ
በል ምራኝ እግሬ... ለካ አዳሬ
አዝኖ ልቤ ሆኖ ስደተኛ በሰው ሀገር
ከሚከፋው በባይተዋር ኑሮ ከሚቸገር
ሸገር ላይ አዲስአበባ
ከትውልዴ ቤት ሀገሬ ልግባ
ሸገር ላይ አዲስአበባ
ከትውልዴ ቤት ሀገሬ ልግባ
ከሀገር የወጣ የራቀ ሰው
ሆኖ ባይተዋር ብሶተኛ
ቀኑ ቀን አይሆን ምን ቢኖረው
ናፍቆት አለበት እንዳይተኛ
እግሬ በስደት ይዞኝ ሄዶ
በሰው ሀገር ላይ ሆኜ እንግዳ
አስተዋሽ የለኝ አይዞህ የሚለኝ
ብርዱም አፈሩም ለኔ ባዳ
ዞሮ ከቤት ኖሮ ከመሬት
ይህ አባባል ይሰጣል ስሜት
በእግሬ ብዞር ብውል ፍለጋ
ለካ አዳሬ ካንቺ ነው ለካ
ለካ አዳሬ... ለካ አዳሬ
ነበር ሀገሬ... ለካ አዳሬ
ከእናት ፍቅሬ... ለካ አዳሬ
በል ምራኝ እግሬ... ለካ አዳሬ
ከአባቴ ሀገር... ለካ አዳሬ
ውሰደኝ ሸገር... ለካ አዳሬ
ከእናት ምድሬ... ለካ አዳሬ
በል ምራኝ እግሬ... ለካ አዳሬ
ከአባቴ ሀገር... ለካ አዳሬ
ውሰደኝ ሸገር... ለካ አዳሬ
ለካ አዳሬ... ለካ አዳሬ
ነበር ሀገሬ... ለካ አዳሬ
ለካ አዳሬ... ለካ አዳሬ
ነበር ሀገሬ... ለካ አዳሬ
ለካ አዳሬ... ለካ አዳሬ
ነበር ሀገሬ... ለካ አዳሬ
ከእናት ፍቅሬ... ለካ አዳሬ
በል ምራኝ እግሬ... ለካ አዳሬ
ከአባቴ ሀገር... ለካ አዳሬ
ውሰደኝ ሸገር... ለካ አዳሬ
ከእናት ምድሬ... ለካ አዳሬ
በል ምራኝ እግሬ... ለካ አዳሬ
ለካ አዳሬ... ለካ አዳሬ
ነበር ሀገሬ... ለካ አዳሬ
ለካ አዳሬ... ለካ አዳሬ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist