Kishore Kumar Hits

Shewandagne Hailu - Min Yilishal lyrics

Artist: Shewandagne Hailu

album: Sik Alegn


ቀለል አርገሽ ያዢ እንጂ ሲወዱሽ አትደነቂ
አለም አይደምቅ ያለ ሰው ቢገባሽ ፍቅርን ብታውቂ
ቀለል አርገሽ ያዢ እንጂ ለፍቅሬ ስጥኝ ምላሽ
ኑሮሽ አይደምቅ ያለ ሰው ቢሳካ ቢያምር ገላሽ
ቢሞላ ኑሮ ቢሳካ ባዶ ነው ፍቅርን ከራቁ
ያለ ሰው መች ይፈታል የዚ አለም ሰም እና ወርቁ
ለፍቅር የተሰራ ልብ እንደ ሰው ላንችም ይዘሻል
ስወድሽ በንፁህ ልቤ ብትወጅኝ ተይ ምን ይልሻል
ምን ይልሻል ብትወጅኝ
ምን ይልሻል ደግሞ
ችሎ ባደሬ ልቤ ባንችው ፍቅር ታሞ
ኧረ ምን አለ ሆዴ
ኧረ ምና አለ
የኔ ቢያረግሽ አንችን እስኪ ምን አለ
ምን ይልሻል ብትወጅኝ
ምን ይልሻል ደግሞ
ችሎ ባደሬ ልቤ ባንችው ፍቅር ታሞ
ኧረ ምን አለ ሆዴ
ኧረ ምና አለ
የኔ ቢያረግሽ አንችን እስኪ ምን አለ
ቀለል አርገሽ ያዥ እንጂ ሲወዱሽ አትደነቂ
አለም አይደምቅ ያለ ሰው ቢገባሽ ፍቅርን ብታውቂ
ቀለል አርገሽ ያዥ እንጅ ለፍቅሬ ስጭኝ ምላሽ
ኑሮሽ አይደምቅ ያለ ሰው ቢሳካ ቢያምር ገላሽ
በኩራት ውበትሽ ታጥሮ ለወዳጅ ግድ እያጣሽ
አጉል ነው ፍቅርን መግፋቱ ያዥ እንጂ ቀለል አረገሽ
በዚህ አለም ለሁሉም ጀራሽ ያለ ሰው ሌላ ምን አለ
ስወድሽ በንፁህ ልቤ ብትወጅኝ ኧረ ምን አለ
ኧረ ምን አለ ሆዴ
ኧረ ምን አለ
የኔ ቢያረግሽ አንችን እስኪ ምን አለ
ምን ይልሻል ብትወጅኝ
ምን ይልሻል ደሞ
ችሎ ባደረ ልቤ ባንችው ፍቅር ታሞ
ኧረ ምን አለ ኧረ ምን አለ
ሚወዱት ሁሉ የራስ ቢሆን ምን አለ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists