Kishore Kumar Hits

The Roha Band - Endegebsu Zala lyrics

Artist: The Roha Band

album: The Reunion


እንደ ገብሱ ዛላ የኔ አለም ፀጉሯ ተጎንጉኖ
መላ ሰውነቷ የኔ አለም በመውደድ ተክኖ
አይነ ኮከብ ጉብል የኔ አለም የደስደስ ጨዋታ
አስተውላኝ ሄደች የኔ አለም የተዋበች ለታ
የዘንድሮ ክረምት አጉረመረመና
ሀምሌና ነሐሴ አዝንቦ ጣለና
አሳየኝ ይሄ አመት ያችን መልከ ቀና
እንዲህም አልነበር የኣቻምና ሀሳቤ
እንዲህም አልነበር የኣቻምና ሀሳቤ
እንደው በቆንጆ ልጅ አሄሄ ተጨነቀ ልቤ
ውበት አይቶ ማለፍ እኔን መች ቸገረኝ
ውበት አይቶ ማለፍ እኔን መች ቸገረኝ
አሸነፈኝ ቃሏ ኣሄሄ ብታመን
እንደ ገብሱ ዛላ የኔ አለም ፀጉሯ ተጎንጉኖ
መላ ሰውነቷ የኔ አለም በመውደድ ተክኖ
አይነ ኮከብ ጉብል የኔ አለም የደስደስ ጨዋታ
አስተውላኝ ሄደች የኔ አለም የተዋበች ለታ
ሸጋ የለም ብየ እውነት ነው ተብሎ
ቆንጆ የለም ብየ እውነት ነው ተብሎ
ጉድ አረገኝ አባይ ጠንበለል አብቅሎ
ሀምሌና ነሐሴ አልፎ አልቆ ወራጁ
ሀምሌና ነሐሴ አልፎ አልቆ ወራጁ
በጋውም ደረሰ ተሸኘች ከምንጩ
ያችስ የፍቅር ሰው ምነው ታዲያ አትመጣም
እያየ በነነ ኣዬ ልቤ እየተቀጣ
እንደ ገብሱ ዛላ የኔ አለም ፀጉሯ ተጎንጉኖ
መላ ሰውነቷ የኔ አለም በመውደድ ተክኖ
አይነ ኮከብ ጉብል የኔ አለም የደስደስ ጨዋታ
አስተውላኝ ሄደች የኔ አለም የተዋበች ለታ
ዘመድ ተሰብስቦ ወገን አለኝ ብየ
ዘመድ ተሰብስቦ ወገን አለኝ ብየ
ቤቱን ባዶ አስቆምኩት ኣዬ ፍሪዳዬን ጥየ
ከሰው መጫወቱን ሆዴ እየተመኘ
ከሰው መጫወቱን ሆዴ እየተመኘ
ደግሞም ከዳ ልቤ ኣሄሄ ወዳንቺ ተሸኘ
አይግጠም ነው እንጂ መቼም ከገጠመ
ልብን በሁዳዴ እየቆረጠመ
የዞረ ያስፈታል ኣሄ የተጠመጠመ
እንደ ገብሱ ዛላ የኔ አለም ፀጉሯ ተጎንጉኖ
መላ ሰውነቷ የኔ አለም በመውደድ ተክኖ
አይነ ኮከብ ጉብል የኔ አለም የደስደስ ጨዋታ
አስተውላኝ ሄደች የኔ አለም የተዋበች ለታ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists