Kishore Kumar Hits

The Roha Band - Akalie lyrics

Artist: The Roha Band

album: The Reunion


አካሌ ሸግዬ ነይ
በምትወጂያት እናት ኦሆ ሰው ጠራኝ ሳትይ
አካሌ ሸግዬ ነይ
ከውበትሽ ጋራ ኦሆ ገለጠ ሰማይ
እንደምን አድረሻል አንቺ ዓመለ ኩሩ
አማለጅ ጠፋልሽ ባገር በመንደሩ
የማብሰልሰል ሚስጥር የሃሳብ ሹክሹክታ
መወያየት ሆኗል ገጥሞ ከትዝታ
መወያየት ሆኗል አዬ ገጥሞ ከትዝታ
የትከሻዬ ቅድ የጫንቃዬ ጌታ
የአይምሮዬ ደባሽ ሸክም የትዝታ
ከየት ያደርሰኛል እግሬስ ብሄድበት
እታትረው ይዤ በትዝታ አቀበት
እታትረው ይዤ አዬ በትዝታ አቀበት
አካሌ ሸግዬ ነይ
ከውበትሽ ጋራ ኦሆ ገለጠ ሰማይ
አካሌ ሸግዬ ነይ
በምትወጂያት እናት ኦሆ ሰው ጠራኝ ሳትይ
ተራመጅ በልቤ በለመድሽው መንገድ
ያንቺማ ትዝታሽ በፀብ አይታገድ
ቢፈርደኝ ምናለ ዳኛ ተሰይሞ
ቂመኛው ልቧማ አጠቃኝ አድኖ
ቂመኛው ልቧማ አዬ አጠቃኝ አድኖ
ፀብቸር አሉኝ አልል ወይ አላድብ ከሰው
እኔስ ያንቺን ፍቅር ወዴት ልካሰሰው
ድረሽ ልቀበልሽ እጆቼን ዘርግቼ
አልካስ በዳኛ አሄ አንቺን አጥቼ
አልካስ በዳኛ አሄ አንቺን አጥቼ
አካሌ ሸግዬ ነይ
በምትወጂያት እናት ኦሆ ሰው ጠራኝ ሳትይ
አካሌ በዳመናው ላይ
ከውበትሽ ጋራ ኦሆ ገለጠ ሰማይ
ከፍቅርሽ ማቅ ወስዶ ልቤን ምን ቀበረው
ትዝታን ጎዝጉዞ ሲያስብሽ ያደረው
እደርሳለሁ እንጂ በየበራበሩ
አንቺ ካልተገኘሽ ምን ሊያምር ነገሩ
አንቺ ካልተገኘሽ አዬ ምን ሊያምር ነገሩ
የለሽ ካጠገቤ አይሎ ትዝታው
ይማፀንሽ ጀመር ምሶሶና ዋልታው
ውበትሽ ተወርቶ ሙግት ተነስቶበት
ተወራርጄአለሁ እንዳልረታበት
ተወራርጄአለሁ አዬ እንዳልረታበት
ይቅር ለምስክር እርቄ መሄዴን
በአካል ድረሺና ልርታልሽ መውደዴን
በአካል ድረሺና ልርታልሽ መውደዴን
በአካል ድረሺና ልርታልሽ መውደዴን
በአካል ደወረሺና ልርታልሽ መውደዴን
በአካል ደወረሺና ልርታልሽ መውደዴን

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists