Kishore Kumar Hits

Hamelmal Abate - Demo Meshe lyrics

Artist: Hamelmal Abate

album: Kemsha


ደሞ መሸ ያ ናፍቆት ሊመጣ
ከኔ ሌላ መሄጃ ላያጣ
ወይ ድካሜን ላያሳርፍልኝ
እንቅልፍ ሆኖ ላያሳልፍልኝ
ምን አድርጊ ይለኛል ለብቻዬ
ያልተመቸኝ አንሶት መኝታዬ
ደሞ መሸ ያ ናፍቆት ሊመጣ
ከኔ ሌላ መሄጃ ላያጣ
ወይ ድካሜን ላያሳርፍልኝ
እንቅልፍ ሆኖ ላያሳልፍልኝ
ምን አድርጊ ይለኛል ለብቻዬ
ያልተመቸኝ አንሶት መኝታዬ

በሽታን እንደራ ማስታመም ነዉ እንጅ
ከማገዝ ይሸሻል በዚህ ቀን ወዳጅ
ጠያቂም አላገኝ አይዞሽ ባይ ሁነኛ
ምን ወገን ሊኖረዉ ወትሮስ ህመምተኛ
አዬ ጉድ የኔስ ፈተና የስንቱን እጅ ያሳየኛል
እያለዉ ለካ ሰዉ ማጣት ከሞትም ሞትን ያስመኛል
አዬ ጉድ የኔስ ፈተና የስንቱን እጅ ያሳየኛል
እያለዉ ለካ ሰዉ ማጣት ከሞትም ሞትን ያስመኛል
አዬ ጉድ የኔስ ፈተና የስንቱን እጅ ያሳየኛል
እያለዉ ለካ ሰዉ ማጣት ከሞትም ሞትን ያስመኛል
ኦሆ ኦሆ ኦሆ ኦሆ
ለታመመማ ሰዉ በሽታዉ ለፀና
የሚያሽል መዲሀኒት መች ያጡለትና
ፍቅር እና ናፍቆት ህመም ለሆነበት
ለእንደኔ አይነቱ ነዉ መላ የጠፋለት
ብቸኝነት ከቦት ከፍቶት ሆድ ለባዉ
ካልፈታዉ እራሱ አስሮት የሄደ ሰዉ
አጃቢ ቢበዛም ሺ ወዳጅ ቢቆጥር
ማን ያፈርስለታል የናፍቆትን አጥር
ለታመመማ ሰዉ በሽታዉ ለፀና
የሚያሽል መዲሀኒት መች ያጡለትና
ፍቅር እና ናፍቆት ህመም ለሆነበት
ለእንደኔ አይነቱ ነዉ መላ የጠፋለት
ብቸኝነት ከቦት ከፍቶት ሆድ ለባዉ
ካልፈታዉ እራሱ አስሮት የሄደ ሰዉ
አጃቢ ቢበዛም ሺ ወዳጅ ቢቆጥር
ማን ያፈርስለታል የናፍቆትን አጥር

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists