Kishore Kumar Hits

Hamelmal Abate - Bayaschilegne lyrics

Artist: Hamelmal Abate

album: Yadelal


ባያስችለኝ ባይሰጠኝም ፈቃድህ
ስማፀንህ ደጅህ ቆሜ በእናትህ
አይምሽብኝ ባዶ ሆኜ እንደገና
አንተዉ ሙላዉ ጎዶሎዬን ፈልግና
እንደገና እንደገና
ጎዶሎዬን ሙላዉ ፈልግና
እንደገና እንደገና
አይምሽብኝ ባዶ ሆኜ መና

መስዉር ጥበብህ ከአንዷ ነብስያዬ
የሰራሃት ህንፃ እቺ አፈር ስጋዬ ገላዬ
እኔነቴን ሆና ከእናቴ ከአባቴ
ተከፍላ ከመጣች ከአለማዊዉ ቤቴ ቤቴ
አሀሀሀ ስንት ዘመን ሆናት ነፍሴ ከራሷ ጋ
አሀሀሀ አንድ ሆና ስትኖር በተፈጥሮ ፀጋ
አሀሀሀ መላዉ ሳይቸግርህ ምላሽ አትንፈጋት
አሀሀሀ ለነፍሴ በልኳ ነፍስያዋን ስጣት
እባክህ እባክህ እባክህ አምላኬ
ስለምንተ ማሪያ ስልህ ተንበርክኬ
መለስ አርገዉና ፊትህን ወደ እኔ
አይተህ ፅደቅብኝ የራሴን ሰዉ ለኔ
እባክህ እባክህ እባክህ አምላኬ
ስለምንተ ማሪያ ስልህ ተንበርክኬ
መለስ አርገዉና ፊትህን ወደ እኔ
አይተህ ፅደቅብኝ የራሴን ሰዉ ለኔ

ባያስችለኝ ባይሰጠኝም ፈቃድህ
ስማፀንህ ደጅህ ቆሜ በእናትህ
አይምሽብኝ ባዶ ሆኜ እንደገና
አንተዉ ሙላዉ ጎዶሎዬን ፈልግና
እንደገና እንደገና
ጎዶሎዬን ሙላዉ ፈልግና
እንደገና እንደገና
አይምሽብኝ ባዶ ሆኜ መና

ትላንትናም ዛሬም ለትልቅ ትንሹ
በረከተ ሰላም ብርሃን በደማቁ
ስታድል እያየሁ ከቀን እስከ ማታ
እኔም ተሰልፌ ባነበርከኝ ቦታ ቦታ
አሀሀሀ እሰይ አሜን አሜን ልበል ጌታዬ
አሀሀሀ ኮቴዋን አሰማኝ ስትረብብ በአልጋዬ
አሀሀሀ ወጋገኗን ልያት ጨረቃን ሸኝታ
አሀሀሀ ይንጋልሽ ስትለኝ ጀንበር የኔን ፋንታ
እባክህ እባክህ በል ፍታልኝማ
አልገለጥ ያለን የቀኑን ጨለማ
ሰምና ወርቅ እንጂ እህ አልፈታኝ ያለዉ
ህብረ ቃሉንማ እኔም ችዬዋለዉ
እባክህ እባክህ እባክህ አምላኬ
ስለምንተ ማሪያ ስልህ ተንበርክኬ
መለስ አርገዉና ፊትህን ወደ እኔ
አይተህ ፅደቅብኝ የራሴን ሰዉ ለኔ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists