Kishore Kumar Hits

Hamelmal Abate - Besemua Eyemale lyrics

Artist: Hamelmal Abate

album: Yadelal


አልችል ያለኝ ልቤ የማይቻል ሲሆን ለመታገስ
ቤቱን ትቼ ወጣሁ ሰዉ ቀረኝም ብዬ ላልመለስ
ደስተኛ ነኝ እኔ ደስተኛ ደስተኛ ብቻዬን ስተኛ
ደስተኛ ነኝ አሁን ብቻዬን ስተኛ
ደስተኛ ነኝ እኔ ደስተኛ ደስተኛ ብቻዬን ስተኛ
ደስተኛ ነኝ አሁን ባላየዉ ዳግመኛ

የትዳር ጓደኛዉ ሆኜ ባለቤቱ
ይገርማል ስሜን መሳሳቴ
ደጋግሞ ሚጠራኝ በተጣት ሚስቱ
ሲጠራኝ በተፋታት ሚስቱ
ይጥራኝ ብዬ እንዳሻዉ ለአፉ እንደቀለለ
ሲጠራኝ አበት ብዬ ሳለ
ደግሞ አሳዝኖኛል በስሟ እየማለ
ሲያወራ በስሟ እየማለ
ተዉኩት ፍቅሩም ከእኔ ወቷል
ልቤማ ከጠላዉ ሰንብቷል
በቃኝ ብታምኑም ባታምኑም
ከእንግዲህ እኔ እሱን አላምንም አልተገናኘንም
ድሮም መጥኜ ብደቁስ
አልኖርም ድስቱን ጥጄ ሳለቅስ
በቃኝ ብታምኑም ባታምኑም
ከእንግዲህ በህልምም በእዉንም አልተገናኘንም

አልችል ያለኝ ልቤ የማይቻል ሲሆን ለመታገስ
ቤቱን ትቼ ወጣሁ ሰዉ ቀረኝም ብዬ ላልመለስ
ደስተኛ ነኝ እኔ ደስተኛ ደስተኛ
ደስተኛ ነኝ አሁን ብቻዬን ስተኛ
ደስተኛ ነኝ እኔ ደስተኛ ደስተኛ
ደስተኛ ነኝ አሁን ባላየዉ ዳግመኛ

ክንዴን አንተርሼዉ ከጐኔ ተኝቶ
ይገርማል ከጐኔ ተኝቶ
የተጣላት ሚስቱን ያናግራል ቃዥቶ
በህልሙ ያወራታል ቃዥቶ
ፊት ሚስቴ ነበረች ተፋተናል ካለ
ከሷ ጋር ተጣልተናል ካለ
ታዲያ እንዴት ልመነዉ በስሟ እየማለ
ሲያወራ በስሟ እየማለ
ተዉኩት ፍቅሩም ከእኔ ወቷል
ልቤማ ከጠላዉ ሰንብቷል
በቃኝ ብታምኑም ባታምኑም
ከእንግዲህ እኔ እሱን አላምንም አልተገናኘንም
ድሮም መጥኜ ብደቁስ
አልኖርም ድስቱን ጥጄ ሳለቅስ
በቃኝ ብታምኑም ባታምኑም
ከእንግዲህ በህልምም በእዉንም አልተገናኘንም
ተዉኩት ፍቅሩም ከእኔ ወቷል
ልቤማ ከጠላዉ ሰንብቷል
በቃኝ ብታምኑም ባታምኑም
ከእንግዲህ እኔ እሱን አላምንም አልተገናኘንም

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists