Kishore Kumar Hits

Madingo Afework - Wsejat lyrics

Artist: Madingo Afework

album: Swedlat, Vol. 3


ውሰጂያት ውሰጂያት
ነፍሴን በስጦታ
ሽልማት እንድትሆን ላንቺ ተበርክታ
ስለሚበልጥብኝ ከኔ የሷ ደስታ
ነፍሴን እንቺ አልኳት
ስለሚበልጥብኝ ከኔ የሷ ደስታ
ነፍሴን እንቺ አልኳት
ቃልሽን አድምጬ በመኖሬ
ቃሌን በመስማትሽ
ከገላዬም በላይ እስትንፋሴ
ትሁን ሽልማትሽ
ፍቅር ቸር ማድረጉ በኛ ታይቶ
ታምኖ ተከበረ
ሰውን የሚያሳሳው ከነፍስ ወዲያ
ሌላ ምን ነበረ
ውሰጂያት እንግዲህ
ውሰጂያት ብያለው
ህይወቴን ልሰጥሽ ተዘጋጅቻለው
አንቺን የጣለልኝ ቸሩ አምላኬ ይክበር
ለኔ ባይልልኝ የት አገኝሽ ነበር
ውሰጂያት ውሰጂያት
ነፍሴን በስጦታ
ሽልማት እንድትሆን ላንቺ ተበርክታ
ስለሚበልጥብኝ ከኔ የሷ ደስታ
ነፍሴን እንቺ አልኳታ
ስለሚበልጥብኝ ከኔ የሷ ደስታ
ነፍሴን እንቺ አልኳት
ፍጹም ጨዋነትሽን ተመልክቼ
ላክብርሽ ማለቴ
ደጋግሜው እንጂ ጥሩነትሽን
መች በአንዴ ሁለቴ
እኔ ለውለታሽ በሽልማት
ነፍሴን ብሰጥሽም
በመናገር እንጂ በማስተዋል
አንቺን አልበልጥሽም
ስትሄጃት እንደኖርሽ
ስኖር አይቻለው
ህይወቴን ልሰጥሽ
ተዘጋጅቻለው ለምኛት እንዳንቺ
ማናት የገዛችኝ
እንቁም ብሩም
አንሷት ህይወት ያሰጠችኝ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists