Kishore Kumar Hits

Madingo Afework - Anchn Beteleye lyrics

Artist: Madingo Afework

album: Swedlat, Vol. 3


ከመገረም ከቃል በላይ
ሰው እንዳንቺ መቼም አላይ
አንቺን ከምንም በላይ በተለየ አይሻለው
ለዘላለም በልቤ ቦታ ሰጥቼሻለው
ከመገረም ከቃል በላይ
ሰው እንዳንቺ መቼም አላይ
አንቺን ከምንም በላይ ከልቤ እውድሻለው
ለዘላለም በውስጤ ቦታ ሰጥቼሻለው
ላንቺ ያለኝ ስሜት ከምንም በላይ ነው
በርቀት ቢለካ ከጨረቃ እጥፍ ነው
አይገልፀውም ቃላት አይገልፀውም አፌ
የፍቅርን ጥልቀት እንዴት አልፌ
አንገቷ ከመቃ በላይ
ወገቧ እህል የማያይ
አይኖቿ ፀሀይ ጨረቃን
ማራኪ ውስጠ ብርሀን
አንቺን በተለየ
አንቺን በተለየ
አንቺን በተላየ
የለም እንደኔ ያየ
አንቺን በተለየ
አንቺን በተለየ
አንቺን በተላየ
የለም እንደኔ ያየ
ከመገረም ከቃል በላይ
ሰው እንዳንቺ መቼም አላይ
አንቺን ከምንም በላይ በተለየ አይሻለው
ለዘላለም በልቤ ቦታ ሰጥቼሻለው
ከመገረም ከቃል በላይ
ሰው እንዳንቺ መቼም አላይ
አንቺን ከምንም በላይ ከልቤ እውድሻለው
ለዘላለም በውስጤ ቦታ ሰጥቼሻለው
ፀባየ መሬት ናት
ፍቅሯ ሞልቶ ሚፈስ
ላይ ውስጧ የሚያምር
አንጀት የምታርስ
ደግነቷ የእናት
ቅንነቷ የልጅ
ውበቷ የመልአክ
መቼም የማያረጅ
ጥርሶቿ ፍፁም የነጡ
ለተአምር የተቀመጡ
ደስታዋ የማያባራ
እሷ ነች ልቧ ተራራ
አንቺን በተለየ
አንቺን በተለየ
አንቺን በተላየ
የለም እንደኔ ያየ
አንቺን በተለየ
አንቺን በተለየ
አንቺን በተላየ
የለም እንደኔ ያየ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists