Kishore Kumar Hits

Madingo Afework - Lalaterf lyrics

Artist: Madingo Afework

album: Swedlat, Vol. 3


ኧረ እንዲያው ነው ላላተርፍ
የደከምኩት ባንቺ ጉዳይ
ክፉ ደጉን እየሰማው
የማልፈው እንዳልሰማው
ኧረ እንዲያው ነው ላላተርፍ
የደከምኩት ባንቺ ጉዳይ
ክፉ ደጉን እየሰማው
የማልፈው እንዳልሰማው
ከሌላ ሰው ባይሽም
ለማመን ይከብደኛል
አፍቃሪሽ ነኝና ሳስበው ያመኛል
ብሰማም ክፉ ነገር
ባንቺ ቂም መች አውቅና
አይሆንም እላለው ወድሻለውና
ታዲያ ምነው ልብሽ እኔን ባይጎዳኝ
ምነው ምነው
ኧረ ነፍሴ ድረስ እስከሚሰማኝ
ምነው ምነው
ኧረ ምነው ልብሽ ለኔ ቢያዝንልኝ
ምነው ምነው
ከምታምኚው በላይ ፍቅር አለብኝ
ምነው ምነው
ኧረ እንዲያው ነው ላላተርፍ
የደከምኩት ባንቺ ጉዳይ
ክፉ ደጉን እየሰማው
የማልፈው እንዳልሰማው
ኧረ እንዲያው ነው ላላተርፍ
የደከምኩት ባንቺ ጉዳይ
ክፉ ደጉን እየሰማው
የማልፈው እንዳልሰማው
ለማንም የማላማሽ ሆንሽና ገበናዬ
ሁሌም ያንቺን ክፉ አይሰማም ጆሮዬ
ብከፋም ለምን ብዬ እራሴን አልጠይቅም
ፍጹም ያንቺን ያህል ሰው ወድጄ አላውቅም
ታዲያ ምነው ልብሽ እኔን ባይጎዳኝ
ምነው ምነው
ኧረ ነፍሴ ድረስ እስከሚሰማኝ
ምነው ምነው
እስኪ ምነው ልብሽ ለኔ ቢያዝንልኝ
ምነው ምነው
ከምታምኚው በላይ ፍቅር አለብኝ
ምነው ምነው
ታዲያ ምነው ልብሽ እኔን ባይጎዳኝ
ምነው ምነው
ኧረ ነፍሴ ድረስ እስከሚሰማኝ
ምነው ምነው
ኧረ ምነው ልብሽ ለኔ ቢያዝንልኝ
ምነው ምነው
ከምታምኚው በላይ ፍቅር አለብኝ
ምነው ምነው

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists