Kishore Kumar Hits

Madingo Afework - Ayhonlgne lyrics

Artist: Madingo Afework

album: Swedlat, Vol. 3


አንድም ቀን ክፉ ቃል ካፏ የማይወጣ
ቅሬታን የማታውቅ ካንደበቷ
ቁጣ ግድ ነው ግድ ይላል እኔ እሷን ብወድ
ሰላሜ ሰላሜ ናት በኔ ማን ሊፈርድ
ሰው በጠፋ ጊዜ ሰው ሆና ተገኝታ
በልቤ ተርፋለች ደሞ በአይኔ ሞልታ
ለምኛት ለመውሰድ እውነትን ተግቼ
ዛሬ ብኖር በሷ ሰላሜን አግኝቼ
ሰላም የምትሰጥ በመውደድ አስራ ነፍሴን ከነፍሷ
ነፍሴን ከነፍሷ
አይሆንልኝም ለአንድ ቀን እንኳን ለመራቅ ከሷ
ለመራቅ ከሷ
አይሆንልኝ እኔስ
አይሆንልኝ
አንድም ቀን ክፉ ቃል ካፏ የማይወጣ
ቅሬታን የማታውቅ ካንደበቷ
ቁጣ ግድ ነው ግድ ይላል እኔ እሷን ብወድ
ሰላሜ ሰላሜ ናት በኔ ማን ሊፈርድ
የደስታ ዘመኔ ከሷ ጋር መጣና
ይኧው ሙሉ አረገኝ እድሌም ተቃና
በሷ ላይ ያቆመው የልቤ ፍለጋ
አብሬያት ዋልኩና ውስጤም ተረጋጋ
ሰላም የምትሰጥ በመውደድ አስራ ነፍሴን ከነፍሷ
ነፍሴን ከነፍሷ
አይሆንልኝም ለአንድ ቀን እንኳን ለመራቅ ከሷ
ለመራቅ ከሷ
አይሆንልኝ እኔስ
አይሆንልኝ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists