Kishore Kumar Hits

Madingo Afework - Keteleyayen lyrics

Artist: Madingo Afework

album: Aydergem ( Ethiopian Contemporary Music)


ከተለያየን ምን አደርጋለሁ እችለዋለው
አብረን ባለን ጊዜ ብዙ አሳልፈን
አይቆጨኝም እኔ እሱ ይበቃኛል
ከተለያየን ምን አደርጋለሁ እችለዋለው
አብረን ባለን ጊዜ ብዙ አሳልፈን
አይቆጨኝም እኔ እሱ ይበቃኛል
እኔ እንደምወድሽ አውቃለሁ ታውቂያለሽ
አንቺዬ አንቺም ታውቂያለሽ
የእህል ውሃ ነገር ምን ታደርጊዋለሽ
ሆድዬ ምን ታደርጊዋለሽ
የመለየት እንባ ፊቴን እያራሰው
አንቺዬ ፊቴን ካራሰው
ልሸኝሽ ጨክኜ የምወድሽን ሰው
ሆድዬ የማምንሽን ሰው
ከእንግዲህ ከጠለቀ ፀሀይ የውስጤ ጀምበር
ጨልሟል የልቤ አዳራሽ እርሜነው ማፍቀር
ሰው ወዶ ሰው እንደመለየት ክፉ ነገር የለም
ልሸኝሽ የመጨረሻዬን በይ ይሁን ግድ የለም
አሃ... አሃ... አሃ
አሃ... አሃ... አሃ
አሃ... አሃ... አሃ
ከተለያየን ምን አደርጋለሁ እችለዋለው
አብረን ባለን ጊዜ ብዙ አሳልፈን
አይቆጨኝም እኔ እሱ ይበቃኛል
ከተለያየን ምን አደርጋለሁ እችለዋለው
አብረን ባለን ጊዜ ብዙ አሳልፈን
አይቆጨኝም እኔ እሱ ይበቃኛል
በሚያስቀና ፍቅር ብዙ አመት ቆየን
ሆድዬ ብዙ ቆየን
ደግ ቀን አዋዶ ክፉ ቀን ለየን
አንቺዬ ክፉ ለየን
ጨክኜ ስሸኝሽ በይ ጨቅነሽ ሂጂ
አንቺዬ ጨክነሽ ሂጂ
ሰው ባለው አይሆንም በእሱ ፍቃድ እንጂ
ሆድዬ በእሱ ነው እንጂ
ቅር ይላል ከሚወዱት ጋራ ጨክነው ሲለዩ
ያቅታል ወደፊት ለመሄድ ወደኋላ እያዩ
ስለይሽ ቅር ቢለው ውስጤ ሸኝቼሽ ስመጣ
ደህና ሁኝ ያለሽ አንደበቴ ለልቤ መልስ አጣ
አሃ... አሃ... አሃ
አሃ... አሃ... አሃ
አሃ... አሃ... አሃ
አሃ... አሃ... አሃ
አሃ... አሃ... አሃ
አሃ... አሃ... አሃ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists