Kishore Kumar Hits

Madingo Afework - Gonder lyrics

Artist: Madingo Afework

album: Aydergem ( Ethiopian Contemporary Music)


ድሮ ቀረ አትበሉ አልቀረም የጥንቱ
እኔስ እመጣለሁ ዛሬም ባርባራቱ
ከመቅደላ ቢሰዋ ህይወቱ
ብዙ ነበር የካሳ ምኞቱ
ላንድነቱ ላንድነቱ
ከአፄ ፋሲል እስከ ቴዎድሮስ
ያፈራችው ጎንደር ትወደስ
ትወደስ ትወደስ
ሳቅ ጨዋታም ልምዴ ነዉ
ብሉ ጠጡልኝ ወጌ ነዉ
እንዲያዉ ወጌ ነዉ ፍቅር ወጌ ነዉ
ጀግንነት ቢሉም ዘሬ ነዉ
ዝናዉ ኩራቱ የኔ ነዉ
ሁሉም የኔ ነዉ ዝናዉ የኔ ነዉ
የአንገት መሀተቤ ጌጤ ነዉ
ሰዉ አክባሪነት ልምዴ ነው
ጎንደሬነቴ ስሜ ነዉ
ኢትዮጵያዊነት ክብሬ ነው
ለኔ ክብሬ ነዉ መመክያዬ ነዉ
እንቁጠር ካላችሁማ የሀገሬን ዉበት
አለኝ ብዙ የምመካበት
እንዘርዝር ካላችሁማ የሀገሬን ዉበት
አለኝ ብዙ የምመካበት
የሀገር አንድነት ሲነሳ
ስሙ አይረሳም የካሳ
የቁራዉ ካሳ ስሙ አይረሳ
ቢያሰጋዉ የነጭ ወረራ
ዳፍት ላይ መድፉን አሰራ
መድፉን አሰራ መድፉን አሰራ
ደብረ ታቦር ቢሉ ዳፋት
ጎንደር የጥበብ ምድር ናት
የእዉቀት ምድር ናት ታሪካዊ ናት
የቀይ ቀበሮ የዋልያ የብርቅ አራዉት መኖርያ
ምቹ መኖርያ ሆና ማደርያ
እንቁጠር ካላችሁማ የሀገሬን ዉበት
አለኝ ብዙ የምመካበት
እንዘርዝር ካላችሁማ የሀገሬን ዉበት
አለኝ ብዙ የምመካበት።

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists