Kishore Kumar Hits

Madingo Afework - Bekagne lyrics

Artist: Madingo Afework

album: Aydergem ( Ethiopian Contemporary Music)


የፍቅር ገዳም ነው ያደለኝ ሰውነት
ናፍቆትን ሰንቆ የሚመንኑበት
የፍቅር ገዳም ነው ያደለኝ ሰውነት
ናፍቆትን ሰንቆ የሚመንኑበት
በእምነት ቃል ተዘርታ
ፀድቃ እድንትለመልም
ነፍሴ አንቺን ትሻለች
ሁሌም በዚች አለም
በእምነት ቃል ተዘርታ
ፀድቃ እድንትለመልም
ነፍሴ አንቺን ትሻለች
ዛሬስ በዚች አለም
በእውነት መአዛ ጠረንሽ
በእውነት አለው ልዩ መስህብ
በእውነት ሳይጠጡ የሚያረካ
በእውነት ሳይበሉ የሚያጠግብ
በእውነት ከአድማስ ክንፍ በላይ
በእውነት ብዙ ዋጋ ያለሽ
በእውነት የሴቶች ናሙና
በእውነት ውድነት ያደለሽ
በእውነት ውድነት ያደለሽ
አይደረግም አይደረግም
ግልፁን ልንገርሽ ያንጀቴን እኔ የስሜቴን
አይደረግም አይደረግም
ግልፁን ልንገርሽ ያንጀቴን እኔ የስሜቴን
ገላዬ ቢታይ አምሮበት ደምቆ
ዐይኔ ቢማትር ከአድማሱ ርቆ
አይደረግም አይ'ደረግም
ባገር በምድሩ ቆንጆ ቢሞላ
አይደረግም ካንቺማ ሌላ
አይደረግም አይደረግም
ገላዬ ቢታይ አምሮበት ደምቆ
ዐይኔ ቢማትር ከአድማሱ ርቆ
አይደረግም አይ'ደረግም
ባገር በምድሩ ሸጋ ቢሞላ
አይደረግም ካንቺማ ሌላ
አይደረግም አይደረግም
የፍቅር ገዳም ነው ያደለኝ ሰውነት
ናፍቆትን ሰንቆ የሚመንኑበት
የፍቅር ገዳም ነው ያደለኝ ሰውነት
ናፍቆትን ሰንቆ የሚመንኑበት
በእምነት ቃል ተዘርታ
ፀድቃ እድንትለመልም
ነፍሴ አንቺን ትሻለች
ሁሌም በዚች አለም
በእምነት ቃል ተዘርታ
ፀድቃ እድንትለመልም
ነፍሴ አንቺን ትሻለች
ዛሬም በዚች አለም
በእውነት የብቸኝነት
በእውነት የትዝታን ገድሎሽ
በእውነት ሀሳብ ትካዜን
በእውነት ከላዬ ላይ ገብተሽ
በእውነት ለጋውን መውደዴን
በእውነት የልቤን ውስጥ እምነት
በእውነት አሳድገሽዋል
በእውነት ህይወት ዘርተሽበት
በእውነት ህይወት ዘርተሽበት
አይደረግም አይደረግም
ግልፁን ልንገርሽ ያንጀቴን እኔ የስሜቴን
አይደረግም አይደረግም
ግልፁን ልንገርሽ ያንጀቴን እኔ የስሜቴን
ገላዬ ቢታይ አምሮበት ደምቆ
ዐይኔ ቢማትር ከአድማሱ ርቆ
አይደረግም አይ'ደረግም
ባገር በምድሩ ቆንጆ ቢሞላ
አይደረግም ካንቺማ ሌላ
አይደረግም አይደረግም
በቃኝ በቃኝ
በቃኝ በቃኝ
በቃኝ በቃኝ
በቃኝ በቃኝ
በቃኝ በቃኝ.

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists