Kishore Kumar Hits

Hibist Tiruneh - Kemeshe Metah lyrics

Artist: Hibist Tiruneh

album: Tetaltenal Wey?...


በሬ ሲንኳኳ ምን መጣ ብዬ
ደጄ ቆመሀል ምነው አንተዬ
አበባ ታቅፈህ መጣህ ለይምሠሉ
አልዘገየህም ወይ ለይቅርታው ቃሉ
ዓይን አወጣብህ ማበሉ
የታዘባችሁ ጉድ በሉ
አንተው ራስህ በድለህ ራስህ ከሰሀል
ካይንህ የገዛ እንባዬን አፍስሰሀል
ሆነህ በደመቀበት በሞቀ አዳሪ
ለእቅፍ የተዘረጋን እጅ ገፍታሪ
የፍቅርን ዋልታ ሠርሳሪ
የመውደድን ጌጥ መንዛሪ
አትራቀኝ ተው ስልህ
በመስቀሉ ስማፀንህ
ህያው ፍቅሬን ረግጠሀል
ዛሬ ምነው ምን ታይቶሀል
ኧኸኸኸኸኸኸ ኧኸኸኸኸኸኸ
ኧኸኸኸኸኸኸ ኧኸኸኸኸኸኸ
በሬ ሲንኳኳ ምን መጣ ብዬ
ደጄ ቆመሀል ምነው አንተዬ
አበባ ታቅፈህ መጣህ ለይምሠሉ
አልዘገየህም ወይ ለይቅርታው ቃሉ
ዓይን አወጣብህ ማበሉ
የታዘባችሁ ጉድ በሉ
ምነው ከመሸ መጣህ ቀኑ ካለፈ
ደጄ ቄጤማው ደርቆ እሾህ ካረፈ
አንተ በአንድ ቃልኪዳን ሁለት ቤት ሠሪ
ምነው ደርሶ መሆንህ ማህተብ አሳሪ
እንደ መስቀል ወፍ በራሪ
በየሞቀበት ዘማሪ
በእንባ ጅረት ርሶ ፊቴ
አይዞሽ የሚል ባጣም ቤቴ
ሠላሜ ነው ቀሪ ሀብቴ
አትንጠቀኝ በእመቤቴ
ኧኸኸኸኸኸኸ ኧኸኸኸኸኸኸ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists