Kishore Kumar Hits

Eyob Mekonen - Negen Layew lyrics

Artist: Eyob Mekonen

album: Ende Kal


ነገን ላየው እጓጓለው
በል ሂድ ዛሬ ጠግቢያለው
ከንግዲህ መቼም ላትመጣ
ደህና ሁን በል ሌላ መጣ
በል ሸኘኝ በሰላም ልሂድ
ልጀምር የነገን መንገድ
ነገን ላየው እጓጓለው
በል ሂድ ዛሬ ጠግቢያለው
ከንግዲህ መቼም ላትመጣ
ደህና ሁን በል ሌላ መጣ
በል ሸኘኝ በሰላም ልሂድ
ልጀምር የነገን መንገድ

ውያለው በትዕግሥት ስጠብቅ ደግነት
ለካስ ለነገ ነው ያለፍኩት ከትላንት
ይምሽልኝ ዛሬ ቀኑ
ያኔ ነው የሚታየው ወጋገኑ
ብርሃን ቢመስልም ዛሬ
አይደለም ብሩህ ቀኔ
ቢጨልም እመርጣለው
ነገን እናፍቃለው
ጨለማው ቢበረታ
ይረታል ነገ ፀሐይ ስትወጣ
ባይኖቼ እስካይ (እጠብቃለሁ)
ባይኖቼ እስካይ (ተስፋን ይዣለሁ)
ባይኖቼ እስካይ (ድቅድቅ ቢሆንም)
ባይኖቼ እስካይ (ጨልሞ አይቀርም)
ባይኖቼ እስካይ (አብሬ አላልፍም)
ባይኖቼ እስካይ (ከዛሬ ጋራ)
ባይኖቼ እስካይ (አላንቀላፋም)
ባይኖቼ እስካይ (የነገን ጮራ)
ነገን ላየው እጓጓለው
በል ሂድ ዛሬ ጠግቢያለው
ከንግዲህ መቼም ላትመጣ ደህና ሁን በል ሌላ መጣ
በል ሸኘኝ በሰላም ልሂድ
ልጀምር የነገን መንገድ
ነገን ላየው እጓጓለው
በል ሂድ ዛሬ ጠግቢያለው
ከንግዲህ መቼም ላትመጣ ደህና ሁን በል ሌላ መጣ
በል ሸኘኝ በሰላም ልሂድ
ልጀምር የነገን መንገድ

ባዶ ቢመስልም ላንተ
በቅቶት የተቆረጠ
አለው የሁሉም ድርሻ
ጨለማውን ማስረሻ
በል በርታ አይቀርም ያንተ
ይመጣል ያንተን በጁ ያካበተ
ተስፋህ ያልተጨበጠ
ሆኖብህ ያዘንክ አንተ
ይሻላል ብትበረታ
ያንተ ቀን እስኪመጣ
ቀን መጥቶ ያጣሀል ታገስ
ዞረው ያጡት ይመጣል ቦታው ድረስ
ባይኖቼ እስካይ (እጠብቃለሁ)
ባይኖቼ እስካይ (ተስፋን ይዣለሁ)
ባይኖቼ እስካይ (ድቅድቅ ቢሆንም)
ባይኖቼ እስካይ (ጨልሞ አይቀርም)
ባይኖቼ እስካይ (አብሬ አላልፍም)
ባይኖቼ እስካይ (ከዛሬ ጋራ)
ባይኖቼ እስካይ (አላንቀላፋም)
ባይኖቼ እስካይ (የነገን ጮ)
ባይኖቼ እስካይ (እጠብቃለሁ)
ባይኖቼ እስካይ (ተስፋን ይዣለሁ)
ባይኖቼ እስካይ (ድቅድቅ ቢሆንም)
ባይኖቼ እስካይ (ጨልሞ አይቀርም)
ባይኖቼ እስካይ (አብሬ አላልፍም)
ባይኖቼ እስካይ (ከዛሬ ጋራ)
ባይኖቼ እስካይ (አላንቀላፋም)
ባይኖቼ እስካይ (የነገን ጮራ)
ባይኖቼ እስካይ
ባይኖቼ እስካይ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists