Eyob Mekonen - Yekunkua Felasefa lyrics
Artist:
Eyob Mekonen
album: Ende Kal
ይገርማል ይገርማል
ተርቦ ልብስ ይደርባል
ይደንቃል ይደንቃል
ተጠምቶ እሳት ይሞቃል
ለመናገር መጎምጀቱ
ለኛስ ነው ወይ መድኃኒቱ
ይገርማል ይገርማል
ተርቦ ልብስ ይደርባል
ይደንቃል ይደንቃል
ተጠምቶ እሳት ይሞቃል
ተጠራርተን ከየቤቱ
ቃልን መርጠን መሻማቱ
ሃምሳ ሎሚ ከብዶት
ይሸከም ጉልበቴ
አታግዙኝ ይቅር
ጌጤ ነው ቅርጫቴ
ለምን አደንቃለው ጥሩ ቃል መራጩን
በምላሱ ስለት የምናብ ቆራጩን
ሁላችን ከሆንን የቋንቋ ፈላስፋ
በተግባር መስካሪ እማኝ እንዳይጠፋ
ምንም ሳይጨበጥ ሳይዳሰስ እንኳ
ጀግና ልንባል ነው ቃልን ካሰካካን
♪
ይገርማል ይገርማል
ተርቦ ልብስ ይደርባል
ይደንቃል ይደንቃል
ተጠምቶ እሳት ይሞቃል
ተጠራርተን ከየቤቱ
♪
ቃልን መርጠን መሻማቱ
ይገርማል ይገርማል
ተርቦ ልብስ ይደርባል
ይደንቃል ይደንቃል
ተጠምቶ እሳት ይሞቃል
ለመናገር መጎምጀቱ
ለኛስ ነው ወይ መድኃኒቱ
አስተዋልኩኝ ብሎ ህመሜን ቢነግረኝ
አላጨበጭብም መድኃኒት ካልሰጠኝ
ለፈለፈው እንጂ መች አጣሁት እኔ
አይራቀቅብኝ እድናለሁ ያኔ
ሁላችን ከሆንን የቋንቋ ፈላስፋ
በተግባር መስካሪ እማኝ እንዳይጠፋ
ምንም ሳይጨበጥ ሳይዳሰስ እንኳ
ጀግና ልንባል ነው ቃልን ካሰካካን
ሃምሳ ሎሚ ከብዶት
ይሸከም ጉልበቴ
አታግዙኝ ይቅር
ጌጤ ነው ቅርጫቴ
ለምን አደንቃለው ጥሩ ቃል መራጩን
በምላሱ ስለት የምናብ ቆራጩን
አስተዋልኩኝ ብሎ ህመሜን ቢነግረኝ
አላጨበጭብም መድኃኒት ካልሰጠኝ
ለፈለፈው እንጂ መች አጣሁት እኔ
አይራቀቅብኝ እድናለሁ ያኔ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist