Kishore Kumar Hits

Eyob Mekonen - Yewinetwan New lyrics

Artist: Eyob Mekonen

album: Ende Kal


ስወድቅም ስነሳ ሳገኝና ሳጣ
አልተለየቺኝም ፍቅሬን አስበልጣ
ሲያጅቡኝ አጫፍራ ሲሸሹኝ አትቀርም
እሷ የእውነቷን ለኔ አትለወጥም
ሲያጅቡኝ አጫፍራ ሲሸሹኝ አትቀርም
እሷ የእውነቷን ለኔ አትለወጥም
ብረባም ባልረባም አይቀርም መውደዷ
ካንገት በላይ ሳይሆን ፍቅሯ ነው ከሆዷ
ብፀዳም ብቆሽሽ እሷ ግድ የላትም
ስማኝ ደስ ይላታል ለውጡ አይታያትም
ትወደኛለች የእውነቷን ነው
ትወደኛለች ከልቧ ነው
ትወደኛለች የእውነቷን ነው
ትወደኛለች እወዳታለሁ
እወዳታለሁ
እወዳታለሁ
ሰዉ እንደጊዜው ይገለባበጣል
እሷ ግን እሷ ናት መውደዴ ገብቷታል
መኖሯን ለምጄ ቸልታ ባበዛ
የልቤን ታውቃለች አትቀየመኝም
መኖሯን ለምጄ ቸልታ ባበዛ
የልቤን ታውቃለች አትቀየመኝም
ብረባም ባረባም አይቀርም መውደዷ
ካንገት በላይ ሳይሆን ፍቅሯ ነው ከሆዷ
ብፀዳም ብቆሽሽ እሷ ግድ የላትም
ስማኝ ደስ ይላታል ለውጡ አይታያትም
ትወደኛለች የእውነቷን ነው
ትወደኛለች ከልቧ ነው
ትወደኛለች የእውነቷን ነው
ትወደኛለች እወዳታለሁ
እወዳታለሁ
እወዳታለሁ
እወዳታለሁ
እወዳታለሁ
እወዳታለሁ
እወዳታለሁ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists