Kishore Kumar Hits

Sami Dan - Qalen - Special Version lyrics

Artist: Sami Dan

album: Roof Top Music (Live Recording Session 1)


ቃሌን
ካንደበቴ የሚወጣው ቃሌ
ይነግርሻል ስለፍቅር ሁሌ
ካልሰማሽው በሌላው ሰንፈሽ
መንገዱ ኃላ እንዳይጠፋሽ
ስሚ ቃልን ብቻ - አንቺ የኔ አቻ
ሌላ ሰው እንዳንቺ የለኝምና
ስሚ ቃሌን ብቻ - የልቤን መክፈቻ
ቁምነገሬን የውስጤን ገበና
ቃሌን ቃሌን እውነታን ይዞ ሚያወጋውን
ልቤን ሚያርሰው
ባማስመሰል ያልተለዋወሰው
ቃሌን ቃሌን ጥሩ መጥፎሽን ሚነግርሽን
ሚወድሽን
ስሚ ቃሌን ብቻ - አንቺ የኔ አቻ
ሌላ ሰው እንዳንቺ የለኝምና
ስሚ ቃሌን ብቻ - የልቤን መክፈቻ
ቁምነገሬን የውስጤን ገበና
ትርጉም አያሻው ሽንገላ
ገልጠሽ ካየሽው በመላ
ሀሳቤን ካላልሽው ችላ
ወስዶ ያሳይሻል ሁሉን
ፍቅሬ ስላንቺ መሆኑን
እውነቱን ከፍቶ ውሉን
እስትንፋሴ
ነሽና አንቺ የራሴ
የምወድሽ እንደነብሴ
እንዳትወድቂ
ቃል እምነቴን ሳጠብቂ
እውነታዬን ሳታውቂ
ስሚ ቃልን ብቻ - አንቺ የኔ አቻ
ሌላ ሰው እንዳንቺ የለኝምና
ስሚ ቃሌን ብቻ - የልቤን መክፈቻ
ቁምነገሬን የውስጤን ገበና

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists