Kishore Kumar Hits

Sami Dan - Kezih Alem - Live lyrics

Artist: Sami Dan

album: Roof Top Music (Live Recording Session 1)


የኑሮ ውጣውረድ ደርሶ ሲይዘኝ
በሆነው ባልሆነው እያስጨነቀኝ
በሀሳብ ሩቅ ሄጄ ስንቱን እኔ ሳስስ
ያው አንቺ ላይ አርፋለው ደርሼ ስመለስ
ፍፁም ሰላም አለ ከአይኖችሽ ላይ
ሁሌም የሚያደርገኝ አንቺን ብቻ እንዳይ
ቀን ልክ እንደ ፀሃይ ማታ እንደጨረቃ
አይኖችሽ ያዩኛል በስስት በሲቃ
ደሞ የሳቅሽ ከኔ ላይ ሚጋባው
ደርሶ እያሳቀኝ ልቤን የሚያሞቀው
ምን አይነት ስጦታ ነሽ አንቺ ልጅ ለነፍሴ
እንድወድሽ ያደረግሽኝ ልክ እኔ እንደራሴ
ከዚህ አለም አንቺ ብቻ ትበቂኛለሽ
ከዚህ አለም አንቺ ብቻ ትበቂኛለሽ
በጄ ላይ ያለው ሁሉ ቢጠፋ ቢወድም አይጨንቀኝም
አንቺ ብቻ አንቺ ብቻ
ሙሉ ማንነቴን ተቀብለሽኛል
ይህ ቀርቷል ይህ ጎሏል መቼ ብለሽኛል
ማመን እስኪያቅተኝ ከጎኔ የሆንሽ
ስንቱን የኔን ጭንቀት ችግሬን ገደልሽ
እኒያ ውብ ቃሎችሽ ከነብይ ሚመስሉት
ገዳዳ ሀሳቤን ስንት ጊዜ አቃኑት
ስንት ድካሞቼ ፍሬ እንዲያፈሩ
እየተንከባከብሻቸው ካንቺው ጋር ነበሩ
በጣም የሚገርመኝ ድንቅ ሀሳቦችሽ
ቢኖሩት ቢኖሩት ማይጠገብ ፍቅርሽ
ከፍጥረታት ልቆ ውበትሽን አያለው
ሁሌ ምፈልገው ካንቺው ጋር መኖር ነው
ከዚህ አለም አንቺ ብቻ ትበቂኛለሽ
ከዚህ አለም አንቺ ብቻ ትበቂኛለሽ
በጄ ላይ ያለው ሁሉ ቢጠፋ ቢወድም አይቆጨኝም
አንቺ ብቻ አንቺ ብቻ
ፍቅር ይተርፈኛል ካንቺ ጋራ ስሆን
ችግር ምናባቱ የመንፈስ ብርሃን አይሆንም
ከዚህ አለም አንቺ ብቻ ትበቂኛለሽ
ከዚህ አለም አንቺ ብቻ ትበቂኛለሽ
በጄ ላይ ያለው ሁሉ ቢጠፋ ቢወድም አይቆጨኝም
አንቺ ብቻ አንቺ ብቻ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists