Kishore Kumar Hits

Sami Dan - Hager Malet lyrics

Artist: Sami Dan

album: Sibet


ሀገር ማለት
ከሞቀው ጎጆ ከሚስት ልጁ ተነጥሎ
ያፈራውን ሁሉ ቀዬ መንደሩን ሁሉን ጥሎ
ከመሰሎቹ ጋ ስንቁን ሸክፎ ቶሎ በል እያለ
የልቡ ላይ እሳት ስሜቱን ቢያንረው እየገነፈለ
ተነሳ እያለ እየተመመ
ተደፈርኩኝ ብሎ በቁጭት ታመመ
ባሳቡ ለሳላት በሆዱ ላዘላት
ሄዶ በቃ ሊሞትላት ከሀሩር ገባላት
ሀገር ማለት ካሳብ የገዘፈች ትልቅ ምታስጠልል ዋርካ ጥላ
ሀገር ማለት ስትኖር ምታኖር ስጠፋ ምንጠፋ ታላቅ ሚስጥር
ሀገር ማለት የትም አለም ስንዞር በልባችንም ውስጥ የምንሸከማት
ሀገር ማለት ከወዛችን ላይ አለች ከገፃችን አለች እኛ ላይ ተስላ
ከጦር ሜዳው ገብቶ ቢጎዳም ግድ የለው
የሷ ፍቅር እንጂ ልቡን ያገዘፈው
ክብሯማ ሲነካ በቁም ከማይ ብሎ
ይሞታል ጀግናዋ አደራ አቀብሎ
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ኢትዮጵያ የተባለችው ሀገር
አንደኛ እናትህ ናት
ሁለተኛ ክብርህ ናት
ሶስተኛ ሚስትህ ናት
አራተኛም ልጅህ ናት
አምስተኛም መቃብርህ ናት
እንግዲህ የእናት ፍቅር የዘውድ ክብር የሚስት የዋህነት
የልጅ ደስታ የመቃብር ከባቢነት እንዲህ መሆኑን እወቅ
ካድማሱ ወዲያ ተሻግሮ ሄዶ ሰው ሀገር ላይ
ሀብት ስልጣኔ ልቡን የሚያሸፍት አይቷል ሲሳይ
የሰማይ የምድር እርቀቱን አይቶ እንዴት ሆነ እያለ
ማነው የጎተተኝ በሚለው ጥያቄ ተብሰለሰለ
ተነሳ እያለ እየተመመ
ተደፈርኩኝ ብሎ በቁጭት ታመመ
ባሳቡ ለሳላት በሆዱ ላዘላት
ሄዶ በቃ ሊሞትላት ከሀሩር ገባላት
ሀገር ማለት በብዙ ሰው ሀሳብ ውስጥ ምትመላለስ ምታብሰለስል
ሀገር ማለት ሲዳብሷት ምትሞቅ መአዛዋ ሚሸት ድንቅ ፍጥረት
ሀገር ማለት ምድራዊ ፍጥረቷ ከዘመን ተሳስሮ ትዝታን የሚያጭር
ሀገር ማለት ቢርቋት የምትቀርብ ሲቀርቧት ምታቅፍ እናት ነገር
መች ሊረሳት ደግሞ ትዝታው ናት ለሱ
ሲመጣ ሚለብሳት እንደ ብርድልብሱ
ሙቀቱም ናትና ለውስጥ ቁርጥማቱ
ወጌሻው ሀኪሙ ለልብ ስብራቱ
አ... ኢትዮጵያ ሀገሬ መመኪያዬ ክብሬ
አ... ኢትዮጵያ ሀገሬ ዞሮ መግቢያዬ በሬ
አ... ኢትዮጵያ ሀገራችን መመኪያ ክብራችን
አ... ኢትዮጵያ ሀገራችን ዞሮ መግቢያ ቤታችን
አ... ኢትዮጵያ ሀገራችን ዞሮ መግቢያ ቤታችን

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists