Sami Dan - Eyangelatagn Newe lyrics
Artist:
Sami Dan
album: Sibet
መሬት የማይነካኝ ባየር ላይ ነጣሪ
ሽቅርቅር አማላይ ነገር አሳማሪ
ከኔ በላይ ማነው ብዬ ምፎክር
ነበርኩ እኔ ላገር ማስቸግር
ወይ ጊዜ ወይ እጣ ክፉ ቢገጥመኝ
ፍቅር ጠልፎ ጥሎ ከቤት አዋለኝ
ትቢቴን አንጥፎ ከመሬት የጣለው
ፍቅርሽማ እያንገላታኝ ነው
ጠዋት እስከ ማታ እያንገላታኝ ነው
ሆነሽ ሁሉም ቦታ እያንገላታኝ ነው
እኔስ ምን ላድርግሽ ውዴ የኔ ገላ
ፍቅርሽማ እያንገላታኝ ነው
የኔ እንዲያ መገንፈል ሀገር ማጥለቅለቁ
አውቀው አሳለፉኝ ቀን እየጠበቁ
በጉልበት ላይ ጉልበት ሲመጣ ድንገት
ያስጨንቃል ያስብላል ወዴት
በሰከነ መንፈስ በረጋው ቃልሽ
ስታነጋግሪኝ ኩራቴን ጥሰሽ
ስንት እርቀት ሄደሽ ነካካሽኝ ይኸው
ፍቅርሽማ እያንገላታኝ ነው
ጠዋት እስከ ማታ እያንገላታኝ ነው
ሆነሽ ሁሉም ቦታ እያንገላታኝ ነው
እኔስ ምን ላድርግሽ ውዴ የኔ ገላ
ፍቅርሽማ እያንገላታኝ ነው
♪
እያንገላታኝ ነው
አቅሜን ያጣሁ ሰው ነኝ አቅሜን አጣሁኝ ዛሬ
አንገቴን እያስደፋኝ ባንቺ ሰው መቸገሬ
አንቺ እንደኔ አይደለሽ እንደኔማ አይደለሽ
ድረሽልኝ በሞቴ ነይ ባክሽ ቶሎ ብለሽ
መዳን ነው ይሉኛል መዳን ነው ይሉኛል ሁሉም
ፍቅር የነካው ሰው ፍቅር ነው ሚወጣው ቃሉ
አንቺን ምክንያት አርጎ ፍቅርማ እኔን ካዳነ
ሁሉንም ልቀበል ልቤም ይሁን የታመነ
ጠዋት እስከ ማታ እያንገላታኝ ነው
ሆነሽ ሁሉም ቦታ እያንገላታኝ ነው
እኔስ ምን ላድርግሽ ውዴ የኔ ገላ
ፍቅርሽማ እያንገላታኝ ነው
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist