Kishore Kumar Hits

Sami Dan - Mengedu Lay lyrics

Artist: Sami Dan

album: Sibet


መንገዱ ላይ
ጃርሰ ቢያ
አባን ቢያ
ጃርሰ ቢያ
ከራኑ አገርሲሳ
ጃለላ ኑወያ
ነጋ ኑወያ
ጃለላ ኑወያ
ኦ... አባን ቢያ
ጃርሰ ቢያ
ኮታ ኑአርፈዳ
ከራኑ አገርሲሳ
ለውጥ ፈልጎ ወጣቱ
ነበረ የወጣው ከቤቱ
ከሩቅ ግን ያገኘችው እሳት
አረገችው ህልሙን እንዳያያት
ተነሰ ብሎ ያስጮኸው ከበላይ
ያልፈዋል የዛን ሰው ሞት ሳያይ
በቁጥር አቅርቦ የሱን ነብስ
ይውላል በነገር ሲናከስ
ታሪኩ ገና ሳያልቅ ተነግሮ
ውሎ ያድራል ሌላውን ገብሮ
አንዲት ነገር ጫፉ ላይ ሳትደርስ
ስንት ይገላል ከቤቱ በምላስ
ቁንጮ ሆኖ የነገር ቃማሪ
የእሳት ጌታ ክብሪት ቀድሞ ጫሪ
ላገር በሚል የማር ቅቢ ቁማር
አሳቀፈን ማንችለውን ችግር
አ... መንገዱ ላይ
መንገዱ ላይ
ስንት ሰው ወደቀ
ኤ... አይበቃንም ወይ እኛ
ጃለላ ኑወያ
ነጋ ኑወያ
ጃለላ ኑወያ
ልብ ካለማ ሚሰማ
ብዙ ነበር እኛን የሚያስማማ
ከፈለግነው መተረማመሱን
ይችሉታል ጥቂጦች ማመሱን
ጥጉን ይዞ መስርቶ ከለላ
መሀል ገብቶ የሚሞተው ሌላ
ካልነቃማ የኛ ሰው በጊዜ
ያጠፋዋል ይሄ ድንዛዜ
ሰፊ መሬት ታላቅ ሀገር ይዞ
በቀን ፀሀይ የጨለማ ጉዞ
እየመራ ገደል ይከተዋል
ማለቂያውን እሱስ መች ያውቀዋል
ካልተገራ ጡንቻማ ምን አውቆ
ያስተክዛል ሀገርን አድቅቆ
አንድ ህይወት ናት አንድ እድል አንድ እጣ
ካስወሰድናት መቼም የማትመጣ
አ... መንገዱ ላይ
መንገዱ ላይ
ስንት ሰው ወደቀ
ኤ... አይበቃንም ወይ እኛ
ጃለላ ኑወያ
ነጋ ኑወያ
ጃለላ ኑወያ
ክቡር ሰው በወንድሙ ታሞ
ይተክዛል ባገሩ ላይ ቆሞ
ጭካኔን ባፉ ውጦ
ወለደ ሞትን ዛሬ አምጦ
አ... መንገዱ ላይ
መንገዱ ላይ
ስንት ሰው ወደቀ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists