Sami Dan - Hagerigna lyrics
Artist:
Sami Dan
album: Asira Andu Getsoche
የዚህ ዘመን ሰው ነኝ
እዚች ምድር ምኖር ከሰው ዘር መገኛ
ሆኜ ነፀብራቋ
ማንነቴ ሁሉ ሀገርኛ
ሀገርኛ ሀገርኛ ሁሉም ባገርኛ
ሀገርኛ ሀገርኛ ሁሉም ባገርኛ
አለም ተከፋፍላ ሁሉም በያገሩ
ከነባህላቸው ባሉበት ሲኖሩ
እኔም አንዱ ሆኜ ከነማንነቴ
የሌላን ሳልነካ ኖርኩኝ እንደ ቤቴ
ሀ ሀ ሀ ሀ ከነነፃነቴ
ሀ ሀ ሀ ሀ ባህሌ ውበቴ
ስጨፍር ስዝናና ሁሉም ባገርኛ
ስጣላም ስታረቅ ሁሉም ባገርኛ
ሰላምታዬም አክብሮቴም ሁሉም ባገርኛ
ሀገርኛ ሀገርኛ ሁሉም ባገርኛ
የሀገሬ ሰው በቅኝ ያልተገዛ
አለው ብዙ ታሪክ ከአፈሩ የበዛ
ተጣልተው ማይችሉት በፍቅር የሚያስሩት
ከነሱ አንዱ ነኝ ሀበሽ የተባልኩት
ሀ ሀ ሀ ሀ ቀርበው የማይርቁት
ሀ ሀ ሀ ሀ ሁልጊዜም የሚያምኑት
ጋብቻዬም አይ ለቅሶዬም ሁሉም ባገርኛ
የማጌጠው የምለብሰው ሁሉም ባገርኛ
ፉከራዬም ሽለላዬም ሁሉም ባገርኛ
ሀገርኛ ሀገርኛ ሁሉም ባገርኛ
(Oromiffa)
ፊደሉም የኔው ነው ቋንቋውም የራሴ
ከኔ ጋራ አድጓል ተጣብቆ ከነፍሴ
ማሙሽና ሚሚ አለ ሚጫወቱት
ከእናት ከአባታቸው ከአያት የወረሱት
ሀ ሀ ሀ ሀ ሁሌም የማይረሱት
ሀ ሀ ሀ ሀ አድገው ሚናፍቁት
ኩኩሉ ፣ አባሮሽ ሁሉም ባገርኛ
እቴ ሜቴ ፣ በዛ በበጋ ሁሉም ባገርኛ
ሆያሆዬ ፣ አበባይሆሽ ሁሉም ባገርኛ
ሀገርኛ ሀገርኛ ሁሉም ባገርኛ
ሀገርኛ ሀገርኛ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist