Sami Dan - Anchin Biye lyrics
Artist:
Sami Dan
album: Asira Andu Getsoche
የማየው ሁሉ በጨለማ ቢዉጠኝ
ልቤ አንቺን እስካገኝ መቼም ቢሆን ተስፋ አልቆርጥም
እያወኩት ፈተናዉ ብዙ እንደሆነ
ልቤ ግን ደሞ እንደሚያገኝሽ በቃ አመነ
አንቺን ብዬ አንቺን ብዬ ጠዋትም ማታ እለፋለው ዬ አንቺን ብዬ አንቺን ብዬ እስከማገኝሽ እደክማለሁ ዬ
አንቺን ብዬ አንቺን ብዬ ቢከፋኝም ቢደላኝም
አንቺን ብዬ አንቺን ብዬ ኦ•••ዬ
°°°°°°
ህልም የሌለው ሰዉ ከፊቱ የሚፈልገዉ
ታዲያ ምንድን ነዉ በዚ አለም ላይ የሚያደርገዉ
ህይወት መንገድ ናት ብዙ ጣጣ ያለባት
የስንቱ ህልም ሀሳብ የሚነጠጥባት
አንቺን ብዬ አንቺን ብዬ ጠዋትም ማታ እለፋለው ዬ አንቺን ብዬ አንቺን ብዬ እስከማገኝሽ እደክማለሁ ዬ
አንቺን ብዬ አንቺን ብዬ ቢከፋኝም ቢደላኝም
አንቺን ብዬ አንቺን ብዬ ኦ•••ዬ
°°°°°°
ቢመስልም ቀኑ ጨለማ
ልቤ ግን ድልን የተጠማ
እረፍት የለኝም አንቺን እስካገኝ
ማንማ አያግደኝ
ቀን ሊነጋ ሲል እንደሚጨልመው
ጊዜያዊ ችግር አቅሜንፈተነዉ
እኔ ብርቱ ሰዉ ለማንም የማልተኛ
ማሸነፊያ ጥበብ አለኛ
አንቺን ብዬ አንቺን ብዬ ጠዋትም ማታ እለፋለው ዬ አንቺን ብዬ አንቺን ብዬ እስከማገኝሽ እደክማለሁ ዬ
አንቺን ብዬ አንቺን ብዬ ቢከፋኝም ቢደላኝም
አንቺን ብዬ አንቺን ብዬ ኦ•••ዬ
ቢመስልም ቀኑ ጨለማ
ልቤ ግን ድልን የተጠማ
እረፍት የለኝም አንቺን እስካገኝ
ማንማ አያግደኝ
ቀን ሊነጋ ሲል እንደሚጨልመው
ጊዜያዊ ችግር አቅሜንፈተነዉ
እኔ ብርቱ ሰዉ ለማንም የማልተኛ
ማሸነፊያ ጥበብ አለኛ
አንቺን ብዬ••••••••ብዬ
አንቺን ብዬ••••••••ብዬ
°°°°°°
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist