Kishore Kumar Hits

Sami Dan - Sint New lyrics

Artist: Sami Dan

album: Asira Andu Getsoche


ሳሚ ዳን ኤንዲ ቤተ-ዜማ

"ከታሰርክበት የህሊና እስራት እስካልዎጣህ ድረስ
እንዳንት በስቃይ የሚማቅቅ አይገኝም
ታሪክህም ካንተ አልፎ ለሰዎች ስለማይጠቅም
መና ነው!
ስለዚህ ሳይመሽብህ ንቃ
የታሰርክበትንም ሰንሰለት በጥሰው
ያኔ ነው ሰው የምትሆነው።"
ስንት ነው?(ስንት ነው?)
ለራስህ የሰጠህው ግምት ዋጋ?(ስንት ነው?)
ስንት ነው?
ስንት ነው?(ስንት ነው?)
ለራስሽ የሰጠሽው ግምት ዋጋ?(ስንት ነው?)
ስንት ነው?
ዛሬ ባለም ላይ የተዘረጋው ልዩ እሰራር
በ ብር፥ በ እውቀት የደከሙትን ኋላ ሚያስቅር
በ ህሊና መገዛትን ጠፍሮ ሚያስር
ለ እውነት ብሎ መኖር በ ምድር ላይ እስኪጠፋ
የ ብዙሃን ኑሮ ሰቆቃው እየከፋ
ሰርቆ መኖር ብቻውን እየተስፋፋ
ይሄ ነው ያንተም አለም ያለህበት
ተጠፍረህ የታሰርክበት

ዋጋ አለህ ወይ ለራስህ ትልቅ ግምት፧
ሰንሰለትህን ምትሰብርበት?
ስንት ነው?(ስንት ነው?)
ለራስህ የሰጠህው ግምት ዋጋ?(ስንት ነው?)
ስንት ነው?
ስንት ነው?(ስንት ነው?)
ለራስሽ የሰጠሽው ግምት ዋጋ?(ስንት ነው?)
ስንት ነው?
ዛሬ ላይ ሆነህ ነገን በ ተስፋ እንዳታየው
በ ሱስ ተጠምደህ ሁሉን ነገር እንድትረሳው
ጠያኪ ትውል መሆንን እንዳትችል ነው
መከበሪያ ማንነትህን ጥለህው
በጂ አዙር በሌሎች ተገዝተሃል
አሳልፈህ አንተ ራስህን ሰጠሃል
ይሄ ነው ያንችም አለም ያለሽበት
ታሪክሽን የረሳሽበት

ዋጋ አለሽ ወይ ለራስሽ ትልቅ ግምት?
ይሄንን ምትፈችበት?
ስንት ነው?

ስንት ነው!?

ስንት ነው?

ሰው ለራሱ ግምት ከሌለው
ኦ ዋጋም የለው!

ሰው ራሱን ካረከሰ
ምኑን ቆሞ ሄደ!

ሰው ካለተማረ አይጠይቅም
አይመራመርም!

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists