ሳሚ ዳን ኤንዲ ቤተ ዜማ
ዝምታዬ መልሶ እኔዉ ላይ ይጮሀል
ይጠይቀኛል
ዝምታዬ መልሶ እኔዉ ላይ ይጮሀል
ያሳድደኛል
ዝምታዬ መልሶ እኔዉ ላይ ይጮሀል
ለምን ዝም አልክ ይለኛል
ዝምታዬ መልሶ እኔዉ ላይ ይጮሀል
የተራበውን አይቼ ሳልፈው
የተጨነቀዉን ሳልሰማው
ለቸገረው ምንም ሳላካፍለው
ለራሴ ብቻ ነው ለካ ምኖረው
ጉልበተኛው ደካማውን ሲረግጠው
ድምፁ እዳይሰማ ሲያደገርዉ
አንድ ቀንም ሳልዋጋለት
ለካ ትቼው ነው ጥዬው ያለፍኩት
ቸልተኝነቴ ለካ በዝቶ ነው ለውጥ የሌለው
ቸልተኝነቴ ለካ አርጎኛል ድምፅ አልባ ሰው
ቸልተኝነቴ ለካ በዝቶ ነው መኖር ያስጠላው
ቸልተኝነቴ ለካ አርጎኛል የዳር ተመልካች ሰው
ድምፅ አልባ ሰው
የዳር ተመልካች ሰው
ራስ ወዳድ ሰው
ድምፅ አልባ ሰው
ዝምታዬ መልሶ እኔዉ ላይ ይጮሀል
ይጠይቀኛል
ዝምታዬ መልሶ እኔዉ ላይ ይጮሀል
ያሳድደኛል
ዝምታዬ መልሶ እኔዉ ላይ ይጮሀል
ለምን ዝም አልክ ይለኛል
ዝምታዬ መልሶ እኔዉ ላይ ይጮሀል
ቁጭት የሚሉት የህመም ጣጣ
ተነስ እያለ ወደኔ መጣ
ሰላማዊ ምድር በል ገንባ እያለ
ከህሊናዬ ሲሟገት ዋለ
አፍንጫን ሲሉት ዐይን እንደሚያለቅሰው
ዛሬ ወንድሜ ቤት ነገ ራሴ ቤት ነው
አርቄ አስቤ ዛሬ ካልተነሳው
ምን አለው ይባላል በቁሜ ሞቻለው
ቸልተኝነቴ ለካ በዝቶ ነው ለውጥ የሌለው
ቸልተኝነቴ ለካ አርጎኛል ድምፅ አልባ ሰው
ቸልተኝነቴ ለካ በዝቶ ነው መኖር ያስጠላው
ቸልተኝነቴ ለካ አርጎኛል የዳር ተመልካች ሰው
በምድር ላይ ሁሉም ዕኩል ካልኖረባት
አንደኛው ጠግቦ ሌላው ከተራበባት
የሀብቱም ልዩነት በጣምም ከሰፋባት
መቼም ይሁን መቼ ሰላም አይኖራት
አፍንጫን ሲሉት ዐይን እንደሚያለቅሰው
ዛሬ ወንድሜ ቤት ነገ ራሴ ቤት ነው
አርቄ አስቤ ዛሬ ካልተነሳው
ምን አለው ይባላል በቁሜ ሞቻለው
ቸልተኝነቴ ለካ በዝቶ ነው ለውጥ የሌለው
ቸልተኝነቴ ለካ አርጎኛል ድምፅ አልባ ሰው
ቸልተኝነቴ ለካ በዝቶ ነው መኖር ያስጠላው
ቸልተኝነቴ ለካ አርጎኛል የዳር ተመልካች ሰው
ድምፅ አልባ ሰው
የዳር ተመልካች ሰው
ራስ ወዳድ ሰው::
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist