Kishore Kumar Hits

Teddy Afro - Atse Tewodros || lyrics

Artist: Teddy Afro

album: Ethiopia


የሰገደላት ዉበቱን
ያቺን የቃል መስታየት
ሞቶ ቀደማት ቴዎድሮስ
ቆሞ ስቃይዋን ላለማየት
የወደቀላት ዉበቱን
ያቺን የቃል መስታየት
ሞቶ ቀደማት ቴዎድሮስ
ቆሞ ስቃይዋን ላለማየት

ኸ... ናና ሲል ናና
ደርሶ ባያስጥለው ገብርዬን ከስለት
ጀግናው ተፈተነ በመቅደላ አቀበት
ተዋከበና ተዋከበና
ወዲህ ዞር ቢል ሰው የለምና
ገብርዬ ሲወድቅ ቀኙ ዛለና
አረሩን ስቦ ጠጣው ያ ጀግና
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና

ኸ... ናና ሲል ናና
ደርሶ ባያስጥለው ገብርዬን ከስለት
ጀግናው ተፈተነ በመቅደላ አቀበት
ተዋከበና ተዋከበና
ወዲህ ዞር ቢል ሰው የለምና
የነደደ እሳት ክንዱን ተርሶ
ጨክኖ ካሳ ጋተና ኮሶ
ሞተ ላንድ አገር ባንዲራ ለብሶ
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና

ካሳ በል አግሳ እንደ አንበሳ
የቕራ አንበሳው ዳግማሮስ ካሳ በል አግሳ
ካሳ በል አግሳ እንደ አንበሳ
ያንዲት እናት ሀገር ክብርዋ ከቶም ሳይረሳ
ካሳ በል አግሳ እንደ አንበሳ
ንቃ በመንፈስ ላንድነት ካሳ ተነሳ
ካሳ በል አግሳ እንደ አንበሳ
አንተ የሞትክላት ሀገር ክብርዋ ሳይረሳ
ካሳ በል አግሳ እንደ አንበሳ
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና
አላይ አለና
ሞተ ወይ ያጀግና

ኦ ናናዬ ነናና ናናዬ-
ናኖ ኦ ፀንነ ይ
ጎንደር ጎንደር የቴዎድሮስ አገር
ያንዲት ኢትዮጵያ ዋልታና ማገር
ነፍሱን የሰጣት ለካ አለም ንቆ
አገር ሊያቆም ነው ቴዎድሮስ ወድቆ
ኸረረረ
ኸረረረ
ኸረረረ
ኸረረረ
አምጡ ቆርጣችሁ ከሹሩባው ላይ
ኪዳን እንሰር እንዳንለያይ
ነፍሱን የሰጣት ለካ አለም ንቆ
አገር ሊያቆም ነው ቴዎድሮስ ወድቆ
ኸረረረ ኸረረረ
ኸረረረ ኸረረረ
አረጀች እያሉ ሰዎቹ ሲያሙሽ
አረጀች እያሉ ሰዎቹ ሲያሙሽ
ሙሽራ ነሽ ጎንደር ይሰፋል ልብስሽ
ተይ ደማ ነይ ደማም
ተይ ደማ ነይ ደማም
ሳይገላገለው ሕልሙን በሆድ ይዞ
ሳይገላገለው ሽሉን በሆድ ይዞ
የሚረዳው አጥቶ ብቻውን ተክዞ
ተክዞ ተክዞ
ስንቱን በሆድ ይዞ
የወገቡን እሳት ከአፎቱ ላይ መዝዞ
የወገቡን እሳት ከአፎቱ ላይ መዝዞ
ጠጥቶላት ሞተ ክንዱን ተንተርሶ
አያሳዝንም ወይ
ኸረረረ
ካሳ ካሳ
የቋራው አንበሳ
ካሳ ካሳ
የቋራው አንበሳ
ዳኘን ዳኘን
አንድ ሕልም አሳየን
ዳኘን ዳኘን
አንድ ሕልም አሳየን
ኦ-ኦ-ኦ-ኦ-ኦ ኦ-ኦ-ኦ-ኦ-ኦ
ኦ-ኦ-ኦ-ኦ-ኦ ኦ-ኦ-ኦ-ኦ-ኦ
ኦ ናናዬ ነናና ናናዬ-
ናኖ ኦ
ዝግባ የሚያሳክለን
አንድ ፍቅር አጥተን
ዝግባ የሚያሳክለን
አንድነትን አጥተን
ከፊት የነበር ነው
ከሰው ኋላ ቀርተን
አናሳዝንም ወይ
ኸረረረ
ጎንደርና ጎጃም ወሎና ትግራይ
ጎንደርና ጎጃም ወሎና ትግራይ
ኦሮሞና ተጉለት ሆነን አንድላይ
ጉራጌና ሐረር ዶርዜ ወላይታ
ቤንሻንጉል ሱማሌ አፋር አሳይታ
ግመሌን ላጠጣት እንደ አፈር ተጉዤ
ግመሌን ላጠጣት ቀይ ባሕር ተጉዤ
አንድ ገመድ አጣሁ ልመልሳት ይዤ
ኸረረረ ኸረረረ
ያንዲት እናት ልጆች መሆናችንን አውቀን
ጎሳና ሐይማኖት ሳይነጣጥለን
ምን ይሳነን ነበር ብንተባበር
አናሳዝንም ወይ
ኸረረረ
ጎንደር ጎንደር የቴዎድሮስ አገር
ላንዲት ኢትዮጵያ ዋልታና ማገር
ነፍሱን የሰጣት ለካ አለም ንቆ
አገር ሊያቆም ነው ቴዎድሮስ ወድቆ
ጎንደር ጎንደር የቴዎድሮስ አገር
ላንዲት ኢትዮጵያ ዋልታና ማገር
ነፍሱን የሰጣት ለካ አለም ንቆ
አገር ሊያቆም ነው ቴዎድሮስ ወድቆ
ጎንደር ጎንደር የቴዎድሮስ አገር
ላንዲት ኢትዮጵያ ዋልታና ማገር
ነፍሱን የሰጣት ለካ አለም ንቆ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists