Kishore Kumar Hits

Teddy Afro - Bado lyrics

Artist: Teddy Afro

album: Arifzefen Singles Collection, Vol. II


ዋሽቶ ለመኖር አፌ አይችልም ከቶ
ታምኖ ይኖራል እንጂ ያለውን በልቶ
ደልቶኝ የሞላ ኑሮ መኖር ባልጠላም
ገንዘብ ለማግኘት ብዬ አላጣም ሰላም
እኔ አላጣም ሰላም አላጣም ሰላም
እኔ አላጣም ሰላም አላጣም ሰላም
ይህ አለም ነዋይ ችሮ ወርቁን በሙዳይ
ማርኮ ከረታት ነፍሴን ከሰጣት ጉዳይ
ህሊና ሲያጣ ሰላም ወርቅ አልማዝ ሞልቶ
ሳይተኙ ማደር ሊሆን ከራስ ተጣልቶ
ከዚህ ሁሉ ቅጣት ይሻላል ማጣት
አስኮንኛት ነፍሴን አልሞላም ኪሴን
ነፍሴ እጅ እንዳትሰጪ ለኪሴ
ታጣይኛለሽ ከራሴ
ሰላሜ እረፍት ያለብሽ መኝታ
ታምነሽ አኑሪኝ ከጌታ
አንገት ከሚሰበር...
ባይበላስ ቢቀር
ያሉት ከሚጠፋ
የወለዱት ይጥፋ
ይሉኝታ ከማጣ
ዛሬ ገንዘብ ልጣ
አስገምቼው ራሴን
አልሞላውም ኪሴን
አንገት ከሚሰበር...
ባይበላስ ቢቀር
ያሉት ከሚጠፋ
የወለዱት ይጥፋ
ይሉኝታ ከማጣ
ዛሬ ገንዘብ ልጣ
አስገምቼው ራሴን
አልሞላውም ኪሴን
አልሞላውም ኪሴን... ባዶ
ባዶ ላርገው ኪሴን... ባዶ
ባዶ ላርገው ኪሴን
አልሞላውም ኪሴን... አሃ
አልሞላውም ኪሴን
ዋሽቶ ለመኖር አፌ አይችልም ከቶ
ታምኖ ይኖራል እንጂ ያለውን በልቶ
ደልቶኝ የሞላ ኑሮ መኖር ባልጠላም
ገንዘብ ለማግኘት ብዬ አላጣም ሰላም
እኔ አላጣም ሰላም አላጣም ሰላም
እኔ አላጣም ሰላም አላጣም ሰላም
ያመል ነው እንጂ ደሃ የገንዘብ የለም
ሰው ባይኖር እያት ራሷ ባዶ ናት አለም
ገንዘብ ብቻ ነው ያለም የዚ አለም ደስታ
ዳግም ይሸጣል ስሞ ቢመለስ ጌታ
ለሰላሳ ዲናር
ሊያጣ ነፍስ ይማር
አስኮንኛት ነፍሴን
አልሞላውም ኪሴን
ነፍሴ እጅ እንዳትሰጪ ለኪሴ
ታጣይኛለሽ ከራሴ
ሰላሜ እረፍት ያለብሽ መኝታ
ታምነሽ አኑሪኝ ከጌታ
አንገት ከሚሰበር...
ባይበላስ ቢቀር
ያሉት ከሚጠፋ
የወለዱት ይጥፋ
ይሉኝታ ከማጣ
ዛሬ ገንዘብ ልጣ
አስገምቼው ራሴን
አልሞላውም ኪሴን
አንገት ከሚሰበር...
ባይበላስ ቢቀር
ያሉት ከሚጠፋ
የወለዱት ይጥፋ
ይሉኝታ ከማጣ
ዛሬ ገንዘብ ልጣ
አስገምቼው ራሴን
አልሞላውም ኪሴን
አልሞላውም ኪሴን... ባዶ
ባዶ ላርገው ኪሴን... ባዶ
ባዶ ላርገው ኪሴን
አልሞላውም ኪሴን... አሃ
አልሞላውም ኪሴን

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists