Kishore Kumar Hits

Teddy Afro - Zelesegna lyrics

Artist: Teddy Afro

album: Arifzefen Singles Collection, Vol. II


ኧኸኸ-ኸ
ምነው ወዳጄ ምነው?
ክበር ተመስጌን የኛ ጌታ
ከጠዋት አንስቶ እስከ ማታ
አብ ልጁን ሰቅሎ: ግብር ጠርቷል
በመድሃኒአለም አዳም ድኗል
የእየሩስአሌም ገዳም ቄስ
አማን ሲል ያድራል ሲቀድስ
ምን አሳሰበው ለእኛ ሰው?
አለም በቃኝ ላለው!
እእኧኧ-ኧ ምነው ወዳጄ ምነው?
አርብ እሮብ: ፆሞ ሲይስቀድስ
ከደጀሰላም ሲመለስ
ብጠራው ዝም አለኝ: ወይ ፍርጃዬ
አቤት አቤቱ ጌታዬ
እኸኸ-ኸ ኸኸ-ኸ ኼ-ኼይ
ኼኼ ና ምነው?
አምላክ ግብር ሰርቶ ያበላል ይላሉ
በምድር ቀሪ የለም: ሁሉም ይጠራሉ
አምላኬ ግብርህን እንዳታሳንሰው
እምቢ ብሎ አይቀርም: አንተ የጠራሃው ሰው
ኤሄሄሄ ና ምነው? ና ምነው? ና ምነው?
እኸኸ-ኸ ኸኸ-ኸ ኼ-ኸይ
ኼኼ ና ምነው?
ቁጠሩ ቢሏቸው: የሳምንቱን ቀናት
ቁጠሩ ቢሏቸው: የሳምንቱን ቀናት
ስድስቱን ጠሩና: እሮብን ገደፏት
ኼኼ ና ምነው: ና ምነው

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists