Kishore Kumar Hits

Teddy Afro - Tarik Tesera (Anbessa) lyrics

Artist: Teddy Afro

album: Arifzefen Singles Collection, Vol. I


መርቆ ሸኝቶ አገር አስይዞ ሰንደቅ አላማ
መርዶ ነው ለወገናችን ማሸነፍ ካቃተንማ
ብሰለፍ ህመሜን ችዬ እሮጬ ላሯሩጣችሁ
ትልቁን እምነት በእናንተ ጥለናል እንግዲህ አይዟችሁ
ከበደኝ ትቼህ ለመግባት ከበደኝ ያውም ያባቴን ከበደኝ በአይኔ ፈለግኩህ ከበደኝ አዙሬ ፊቴን
በል ፍጠን ድሉ ናፍቆታል በል ፍጠን ጓጉታል ወገኔ
በል ፍጠን እንዳትሸነፍ በል ፍጠን አትይ ወደኔ
አልሆንልህ አለኝ እኔ አልሆንልህ አለኝ
አንተን ጥሎ መግባት ሃይሌ አልሆንልህ አለኝ
አልሆንልህ አለኝ እኔ አልሆንልህ አለኝ
አንተን ጥሎ መግባት ሃይሌ አልሆንልህ አለኝ
አንበሳ አንበሳ
ቀነኒሳ አንበሳ
ታሪክ ሰራ አንበሳ የማይረሳ
አንበሳ ቀነኒሳ
አንበሳ ቀነኒሳ
አንበሳ ቀነኒሳ
አደራ የአቅሜን ሰራሁኝ አደራ እኔ ላገሬ
አደራ የ፭ የ፲ ሺህ በኦሎምፒክ ልሸኝ ነው ዛሬ
እዮሃ ከባንዲራው ነው እዮሃ ቃልኪዳናችን
እዮሃ አታፍርም በኛ እዮሃ ሃይሌ አባታችን
አልሆንልህ አለኝ እኔ አልሆንልህ አለኝ እኔ
አንተን ጥሎ መግባት ሃይሌ አልሆንልህ አለኝ እኔ
አለልህ ስለሺ ደጀን በርታ ቀነኒሳ
ይልቅ አሸንፈህ ቶሎ ባንዲራውን አንሳ
አልሆንልህ አለኝ እኔ አልሆንልህ አለኝ እኔ
አንተን ጥሎ መግባት ሃይሌ አልሆንልህ አለኝ እኔ
አለልህ ስለሺ ደጀን በርታ ቀነኒሳ
አንተ ነህ ያሁኑ ዘመን ተተኪው አንበሳ
አንበሳ ቀነኒሳ
አንበሳ ቀነኒሳ
አንበሳ
ታሪክ ሰራ አንበሳ የማይረሳ
አንበሳ ቀነኒሳ
አንበሳ ቀነኒሳ
አንበሳ ቀነኒሳ
እዮሃ ጉሮ ወሸባዬ እዮሃ ታሪክ ሰራችሁ
እዮሃ ያገሬ ልጆች እዮሃ ኑ ልቀፋችሁ
እዮሃ በል አንሳ ፎቶ እዮሃ ለብሰን ባንዲራ
እዮሃ ብለህ ፃፍበት እዮሃ "ታሪክ ተሰራ"
እልል በል ያገሬ ጎበዝ ለእምዬ ውለታ
ወርቅ አመጣሁላት እኔ ለክብሯ ስጦታ
በል ኩራ ያዝና በአፍህ የባንዲራ ዘንግ
ብር አመጣሁላት እኔ ለእምዬ ማዕረግ
እልል በል ያገሬ ጎበዝ ለእምዬ ውለታ
ወርቅ አመጣሁላት ልጇ ለክብሯ ስጦታ
አንበሳ ቀነኒሳ
አንበሳ ቀነኒሳ
(አንበሳ) እዩት ንጉሱን (አንበሳ) ግርማ ሞገሱ
(አንበሳ) ሰው ብር ሸለመው (አንበሳ) ሰጠው ላደመሱ
(አንበሳ) ይቺ ባንዲራ (አንበሳ) ናት እድለኛ
(አንበሳ) ዛሬም አኮራት (አንበሳ) ቀነኒኬኛ
(አንበሳ) ቀነኒኬኛ
(አንበሳ) ናት እድለኛ
አንበሳ አንበሳ
አንበሳ አንበሳ
አንበሳዬ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists