Kishore Kumar Hits

Teddy Afro - Bel Stegn lyrics

Artist: Teddy Afro

album: Yasteseryal


ምነው ብትሰማኝ አምላኬ
ፈልገህ ብትሰጠኝ ሰው በልኬ
እኔ አጣሁ ፈልጌ
ምነው ብትሰማኝ ፈጣሪ
መርቀህ ብትሰጠኝ አንድ አፍቃሪ
ከኔ ጋር ነዋሪ

ብዙ ዘመን
ስባክን ከርሜ ሰው ፍለጋ
ዞሬ መጣሁ
ዘዴ ካለህ ብዬ ወዳንተ ጋር
የሞከርኩት
አልሆንልህ አለኝ እውነተኛ
ያሰብክልኝ
ሰው እንዳለ ለኔ በል ስጠኛ
ላይ ሳይ! አይኔን አንስቼ
ላይ ሳይ! ወዳለህበት
ላይ ሳይ! ጭንቄን ብትሰማኝ
ላይ ሳይ! ተው ምናለበት
ላይ ሳይ! የፈጠርካትን
ላይ ሳይ! የአዳም መከታ
ላይ ሳይ! የእናቴን ምትክ
ላይ ሳይ! ተው ስጠኝ ጌታ
ላይ ሳይ!
አምላኬ (በል ስጠኝ!)
ሰው በልኬ (በል ስጠኝ!)
አምላኬ (በል ስጠኝ!)
ሰው በልኬ (በል ስጠኝ!)
አምላኬ (በል ስጠኝ!)
ሰው በልኬ)በል ስጠኝ!)
በል ስጠኝ!
በል ስጠኝ!
ምን ይሳንሀል (በል ስጠኝ!)
ሁሉ በእጅህ (በል ስጠኝ!)
ስማኝ ስጠራህ (በል ስጠኝ!)
እኔ ልጅህ (በል ስጠኝ!)
አምላኬ (በል ስጠኝ!)
ሰው በልኬ (በል ስጠኝ!)
አ አምላክ (በል ስጠኝ!)
ሰው በልክ (በል ስጠኝ!)
አ አምላክ (በል ስጠኝ!)
ሰው በልክ (በል ስጠኝ!)
በል ስጠኝ!

ምነው ብትሰማኝ አምላኬ
ፈልገህ ብትሰጠኝ ሰው በልኬ
እኔ አጣሁ ፈልጌ
ምነው ብትሰማኝ ፈጣሪ
መርቀህ ብትሰጠኝ አንድ አፍቃሪ
ከኔ ጋር ነዋሪ

በዚች ዓለም
ምነው ለኔ ብቻ ጠፋ አፍቃሪ
ሰው እያለ
ባይተዋር አታርገኝ ተው ፈጣሪ
ከአፈሩ ላይ
የሰራሃት ነፍሴ ናት ብቸኛ
ያሰብክልኝ
ሰው እንዳለች ለኔ በል ስጠኛ
ላይ ሳይ! አይኔን አንስቼ
ላይ ሳይ! ወዳለህበት
ላይ ሳይ! ጭንቄን ብትሰማኝ
ላይ ሳይ! ተው ምናለበት
ላይ ሳይ! የፈጠርካትን
ላይ ሳይ! የአዳም መከታ
ላይ ሳይ! የእናቴን ምትክ
ላይ ሳይ! ተው ስጠኝ ጌታ
ላይ ሳይ!
አምላኬ (በል ስጠኝ!)
ሰው በልኬ (በል ስጠኝ!)
አምላኬ (በል ስጠኝ!)
ሰው በልኬ (በል ስጠኝ!)
አምላኬ (በል ስጠኝ!)
ሰው በልኬ (በል ስጠኝ!)
በል ስጠኝ!
በል ስጠኝ!
ምን ይሳንሀል (በል ስጠኝ!)
ሁሉ በእጅህ (በል ስጠኝ!)
ስማኝ ስጠራህ (በል ስጠኝ!)
እኔ ልጅህ (በል ስጠኝ!)
አምላኬ (በል ስጠኝ!)
ሰው በልኬ (በል ስጠኝ!)
አ አምላክ (በል ስጠኝ!)
ሰው በልክ (በል ስጠኝ!)
አ አምላክ (በል ስጠኝ!)
ሰው በልክ (በል ስጠኝ!)
በል ስጠኝ!
ምን ይሳንሀል (በል ስጠኝ!)
ሁሉ በእጅህ (በል ስጠኝ!)
ስማኝ ስጠራህ (በል ስጠኝ!)
እኔ ልጅህ (በል ስጠኝ!)
አምላኬ (በል ስጠኝ!)
ሰው በልኬ (በል ስጠኝ!)
አ አምላክ (በል ስጠኝ!)
ሰው በልክ (በል ስጠኝ!)
አምላኬ (በል ስጠኝ!)
ሰው በልኬ (በል ስጠኝ!)
አ አምላክ (በል ስጠኝ!)
ሰው በልክ (በል ስጠኝ!)

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists