Kishore Kumar Hits

Teddy Afro - Etege lyrics

Artist: Teddy Afro

album: Yasteseryal


ኧረ ባላቅሽ ከምጨነቅ አንቺን ወድጄ
ኖሬ ምድር ላይ ገና አለሜን ምኑን አውቄ
ፍቅርን ልቻለው ደሞ በምን ጉልበቴ
አቤት እያልኩኝ ሁሌም ለእመቤቴ
ኧረ ባላቅሽ ከምጨነቅ አንቺን ወድጄ
ኖሬ በደላኝ ገና አለሜን ምኑን አውቄ
ፍቅርን ልቻለው ደሞ በምን ጉልበቴ
አቤት እያልኩኝ ሁሌ ለእመቤቴ

ለጉድ አሳምሯት ምትኳ እንዳይገኝ
ጥሎኛል ከጇ ላይ እንዳሻት ታድርገኝ
በምን ይኮነናል ቢጠየቅስ ነብሷ
የሸጠኝ ፍቅር ነው የገዛቺኝ እሷ
ለጉድ አሳምሯት ምትኳ እንዳይገኝ
ጥሎኛል ከጇ ላይ እንዳሻት ታድርገኝ
በምን ይኮነናል ቢጠየቅስ ነብሷ
የሸጠኝ ፍቅር ነው የገዛቺኝ እሷ
እንዴት ልኩራበት በወንድነቴ
አቤት እያልኩኝ ለእመቤቴ
የፍቅር ንጉስ የፍቅር ጌታ
እኔ ሎሌ ነኝ እሷ ብላት
ከረታኝ ፍቅርሽ ምን አደርጋለሁ
አላለልኝም እችለዋለሁ
አላለልኝም እችለዋለሁ
አላለልኝም እችለዋለሁ

ኧረ ባላቅሽ ከምጨነቅ አንቺን ወድጄ
ኖሬ በደላኝ ገና አለሜን ምኑን አውቄ
ፍቅርን ልቻለው ደሞ በምን ጉልበቴ
አቤት እያልኩኝ ሆሌ ለእመቤቴ
ኧረ ባላቅሽ ከምጨነቅ አንቺን ወድጄ
ኖሬ በደላኝ ገና አለሜን ምኑን አውቄ
ፍቅርን ልቻለው ደሞ በምን ጉልበቴ
አቤት እያልኩኝ ሆሌ ለእመቤቴ

ካቢኔው የፍቅሬ ልብ ነው ዙፋኑ
እንዲህ አይደለምወይ ወደው ሲታመኑ
ሹም እንዳዘዘው ሰው አጎንብሼ መሬት
ሰጠራኝ አቤት ነው ስትልከኝ ወዴት
ተጣሩ እቴጌ አቤት በል አሽከር
ወደህ በገባህ አትከራከር
ወዶ ለገባ በቴጌ ቤት
አዲስ አደለም አቤት ማለት
ክብሬ ተነካ ሳትል ማረጌ
አቤት ብቻ ነው ሲጣሩ እቴጌ
አላለልኝም እችለዋለሁ
አላለልኝም እችለዋለሁ

እቴጌ (አቤት አቤት)
እቴጌ (አቤት አቤት)
እቴጌ አሀዬዬ እቴጌ አሀሀ
እቴጌ አሀዬዬ እቴጌ አሀሀ
እቴጌ አሀዬዬ እቴጌ አሀሀ
እቴጌ አሀዬዬ እቴጌ አሀሀ
እቴጌ አሀዬዬ እቴጌ አሀሀ
እቴጌ አሀዬዬ እቴጌ አሀሀ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists