Kishore Kumar Hits

Ephrem Tamiru - Mulu Gojam lyrics

Artist: Ephrem Tamiru

album: Huala Endaykocheshe (Ethiopian Contemporary Music)


እስኪ ስም ላዉጣልሽ አሄ
ሙሉ ጐጃም ብዬ ሙሉ ጐጃም ብዬ
አድሎሻል ሁሉን አሄ ከሰዉ የተለየ
እስኪ ስም ላዉጣልሽ አሄ
ሙሉ ጐጃም ብዬ ሙሉ ጐጃም ብዬ
አድሎሻል ሁሉን አሄ ከሰዉ የተለየ
አድሎሻል ሁሉን አሄ ከሰዉ የተለየ
ገና በአይኔ ሳይሽ ከልቤ ገባሽ
ይሄን የሰዉ መወደድ ማነዉ የቀባሽ
እንደ ሐገርሽ ቅኔ ፍቅርሽ እያናፋ
የሚያስብሽ እንጂ የሚያገኝሽ ጠፋ
ፈልጌ ፈልጌ እንከን ባጣብሽ
ሙሉ ጐጃም አልኩሽ ያልጐደለብሽ
ተቀማጥለሽ አድገሽ ጎጃም ላይ
ምኔን ልስጥሽ ከፍቅር በላይ
አድርጐሻል እንደዉ የበላይ
የዋሸራን ቅኔ እየዘረፍሽ
ሰምና ወርቅ ሆነና ፍቅርሽ
እንደዋዛ አትገኝ ተባልሽ
ኦሆ ነይ ደሞ ነይ ደሞን
ነይ ደሞ ነይ ደሞን
ነይ ደሞ ነይ ደሞን
ኦሆ ነይ ደሞ ነይ ደሞን
ነይ ደሞ ነይ ደሞን
ነይ ደሞ ነይ ደሞን
ነይ ደሞ ነይ ደሞ ነይ ደሞ ነይ ደሞ
ነይ ደሞ ነይ ደሞ ነይ ደሞ ነይ ደሞ
ፍቅርሽን ለኩራት ለገድ ቢመኙት
ዘርሽን ፈልገዉ ጐጃም አገኙት
በአባይና ጣና ዋኝተሸ ማደግሽ
ወይስ የዋሸራ ቅኔ መዝረፍሽ
ወይስ ከነ በላይ የዘር ሀረግሽ
ምን ይሆን እነደዚህ የሚያስወድድሽ

እስኪ ስም ላዉጣልሽ አሄ
ሙሉ ጐጃም ብዬ ሙሉ ጐጃም ብዬ
አድሎሻል ሁሉን አሄ ከሰዉ የተለየ
እስኪ ስም ላዉጣልሽ አሄ
ሙሉ ጐጃም ብዬ ሙሉ ጐጃም ብዬ
አድሎሻል ሁሉን አሄ ከሰዉ የተለየ
አድሎሻል ሁሉን አሄ ከሰዉ የተለየ
# INSTRUMENTAL
ዛላሽ አበባ ነዉ ፍቅርሽ የጠበቀ
ለስንቱ የሚበቃ ዉበት በአንቺ አለቀ
ሞልቶ እንደተረፈ ሰብሽ በየሜዳ
ፍቅርም ይታፈሳል አሉ ከአንቺ ጓዳ
ስንቱ ደጅ ይጠናል የአንቺን ፍቅር ብሎ
ትችያለሽ አንቺ መኖር ተቻችሎ አዬዬ ተቻችሎ
ያየሽ ሁሉ ስትሄጅ በመንደር
ከየት ይሆን ሲል ሲወራረድ
እኔ አወኩሽ በአንገትሽ ግማድ
ዉብ ሸጋ ናት ቆንጅዬ መባሉ
ለመጠራት እያነሰሽ ቃሉ
ሙሉ ጐጃም ይልሻል ሰዉ ሁሉ
ኦሆ ነይ ደሞ ነይ ደሞን
ነይ ደሞ ነይ ደሞን
ነይ ደሞ ነይ ደሞን
ኦሆ ነይ ደሞ ነይ ደሞን
ነይ ደሞ ነይ ደሞን
ነይ ደሞ ነይ ደሞን
ነይ ደሞ ነይ ደሞ ነይ ደሞ ነይ ደሞ
ነይ ደሞ ነይ ደሞ ነይ ደሞ ነይ ደሞ
ለእናትና አባትሽ ምንጭ ነሽ ልቻል
ከአልማዝ ከዕንቁ በላይ ፍቅርሽ ይበልጣል
ማኛ ነጭ ጤፉን እንዳልሰፈንሽ
ለሰዉ ትተርፊያለሽ እንኳን ለራስሽ
በአባይና ጣና ዋኝተሸ ማደግሽ
ወይስ የዋሸራ ቅኔ መዝረፍሽ
ወይስ ከነ በላይ የዘር ሀረግሽ
ምን ይሆን እነደዚህ የሚያስወድድሽ
የዋህ ልቤን ይዤ ልጓዝ ልገስግሰዉ
ፍቅር ይገለዋል መቼም የጐጃም ሰዉ
ፍቅር ይገለዋል መቼም የጐጃም ሰዉ
ፍቅር ይገለዋል መቼም የጐጃም ሰዉ
አቤት አቤት አቤት አቤት አቤት አቤት

ኦሆ ነይ ደሞ ነይ ደሞን
ነይ ደሞ ነይ ደሞን
ነይ ደሞ ነይ ደሞን
ኦሆ ነይ ደሞ ነይ ደሞን
ነይ ደሞ ነይ ደሞን
ነይ ደሞ ነይ ደሞን
ኦሆ ነይ ደሞ ነይ ደሞን
ነይ ደሞ ነይ ደሞን
ነይ ደሞ ነይ ደሞን
አቤት አቤት አቤት አቤት አቤት አቤት

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists