Kishore Kumar Hits

Ephrem Tamiru - Walshesa Baynie lyrics

Artist: Ephrem Tamiru

album: Huala Endaykocheshe (Ethiopian Contemporary Music)


ልቤም ይሰወራል በናፍቆት ተሰርቆ
መቼም አይመቸው ሰው ከሀገሩ ርቆ
ስንቱን ባሕር አልፎ ዐይንሽ ካይኔ የዋለው
ሰው ፈልጎ እንዳጣ ወገን እንደሌለው
ባይኔ ላይ ዋልሽሳ ባይኔ
ባይኔ ላይ ዋልሽሳ ባይኔ
ክፉ አመል አስለምደሽኝ
ትዝታ ሆንሽብኝ ለእኔ
ባይኔ ላይ ዋልሽሳ ባይኔ
ባይኔ ላይ ዋልሽሳ ባይኔ
ምን ነክቶሽ ይሆን እያልኩኝ
በሀሳብ አለቀ ጎኔ
ትዝታ ሆንሽብኝ ለእኔ
በሀሳብ አለቀ ጎኔ
ቻይው ናፍቆትሽን ብለሽ በርታ ፀና
ብለሽ በርታ ፀና ብለሽ በርታ ፀና
መልሶ እስኪያመጣኝ ያራቀኝ ጎዳና
ያራቀኝ ጎዳና ያራቀኝ ጎዳና
ከሀገር የሚወጣ ቢባል ተሰደደ
ቢባል ተሰደደ ቢባል ተሰደደ
ግድ ሆኖበት እንጂ ማን የሰው ወደደ
ማን የሰው ወደደ ማን የሰው ወደደ
በቃ ሲለዉ የኔን ማዘን
እወጣለዉ ከመባዘን
ከመናፈቅ ያኔ አርፋለሁ
እስከዚያው ቀን በተስፋ አለሁ
መጥቆር መክሳት ማዘን ትተሸ
ብጠብቂኝ ተበራትተሽ
ሁሉም ያልፋል ከቻልን አሁን
ብቻ እስከዚያው ደህና እንሁን
ልቤም ይሰወራል በናፍቆት ተሰርቆ
መቼም አይመቸው ሰው ከሀገሩ ርቆ
ስንቱን ባሕር አልፎ ዐይንሽ ካይኔ የዋለው
ሰው ፈልጎ እንዳጣ ወገን እንደሌለው
ባይኔ ላይ ዋልሽሳ ባይኔ
ባይኔ ላይ ዋልሽሳ ባይኔ
ክፉ አመል አስለምደሽኝ
ትዝታ ሆንሽብኝ ለእኔ
ባይኔ ላይ ዋልሽሳ ባይኔ
ባይኔ ላይ ዋልሽሳ ባይኔ
ምን ነክቶሽ ይሆን እያልኩኝ
በሀሳብ አለቀ ጎኔ
ትዝታ ሆንሽብኝ ለእኔ
በሀሳብ አለቀ ጎኔ
አንቺስ ወገን አለሽ ሲያዝኑ የሚያፅናና
ሲያዝኑ የሚያፅናና ሲያዝኑ የሚያፅናና
እኔማ ከፋኝ ብል የት እሄደውና
የት እሄደውና የት እሄደውና
ከአንቺማ ብመጣ መንፈሴም ባረፈ
መንፈሴም ባረፈ መንፈሴም ባረፈ
በወጣልኝ ናፍቆት እየተቀረፈ
እየተቀረፈ እየተቀረፈ
ምን ቢከፋው የራቀ ሰው
ወሳጅ እግሩን ሲመልሰው
ይፅናናዋል ሲያገኝ ሁሉን
እስከጊዜው ሰላም ያርገን
መጥቆር መክሳት ማዘን ትተሸ
በጠበቅሺኝ ተበራትተሽ
ሁሉም ያልፋል ከቻልን አሁን
ብቻ እስከዚያው ደህና እንሁን
ምን ቢከፋዉ የራቀ ሰው
ወሳጅ እግሩን ሲመልሰው
ይፅናናዋል ሲያገኝ ሁሉን
እስከጊዜው ሰላም ያርገን
መጥቆር መክሳት ማዘን ትተሸ
በጠበቅሺኝ ተበራትተሽ
ሁሉም ያልፋል ከቻልን አሁን
ብቻ እስከዚያው ደህና እንሁን

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists