Kishore Kumar Hits

Ephrem Tamiru - Alader Tegneche lyrics

Artist: Ephrem Tamiru

album: Yehese Ken Balefe, Vol. 10


ጀንበሯን ለማታ ሸኝቼ
ኮከብ እቆጥራለሁ ወጥቼ
መቼም አላድር ተኝቼ
እንዴት ይንጋልኝ ጓጉቼ
ወዲያ ባይ የለችም ከማዶ
ወዲህ ሲያር አንጀቴ ተማግዶ
ሀሳቤም አይተኛም ተሰዶ
ባይኔ ብዳስስ ከአድማስ ሰማይ
የታለች እኔ እሷንም አላይ
ጠፈር ካለችው ከዚያች ጨረቃ
አለች አልታይ ወዳጄ ርቃ
አሁን መች ይቀራል ሳይገባት መውደዴ
በፍቅሯ መንደዴ
ሲመጣ በፍቅር ማህበር መጠጫዋ
ሲደርሳት ፀበሉ የት ይሆን መውጫዋ
መስሏት የማትቀርብ ወዳም ማትሰዋ
ሲደርሳት ፀበሉ የት ይሆን መውጫዋ
ወዴት ትደርስ ያኔ ስትቀምስ ያንን ፅዋ
ዋ.ዋ.ዋ.ዋ ዋ
ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ ዋይ ስትቀምስ ያንን ፅዋ
ሆዴን ሲያጋየው የእርሷ ትዝታ
እሳት ይጭራል ደርሶ ለ ማታ
ቀናት በኔ ላይ ፍቅሯ በረታ
ይብላኝ ያለእርሷ ላጣው መከታ
የማጣት ቁጭቱን እረመጡን ጭሮ
ቢቃጠል አይሸታት ሆዴ ተንጨርጭሮ
ልቤ እንዲህ ሲቃጠል ላይቀናው ሰው ወዶ
ሲጨሰው ይደርሳል በሀሳብ ወዲያ ማዶ
ወይ ማዶ
ወይ ማዶ
ልቤ እኔን ክዶ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists