Kishore Kumar Hits

Ephrem Tamiru - Ye-Chat lyrics

Artist: Ephrem Tamiru

album: Yehese Ken Balefe, Vol. 10


ታድሏል አካሌ ይዟል ድርሻውን
ታድሏል አካሌ ይዟል ድርሻውን
ብቻ ያዝልቅልን መጨረሻውን
ታድሏል አካሌ ይዟል ድርሻውን
ታድሏል አካሌ ይዟል ድርሻውን
ብቻ ያዝለቅልን መጨረሻውን
ብንገናኝ አንድ ቀን ተዋውቀን
ይኸው አለን ተደስተን ስቀን
ምንም ሳይቀርባት ሞልታ ደረሰችኝ
ለልቤ አልጎደለች ላይኔ አላነሰችኝ
ለፍቅሬ ፍቅር አየሁ ላሳቤ መፅናኛ ለአካሌ ዘመዴ
ተስፋ ሰጥቶ ደላኝ በሷ ጊዜ ተመቸው መውደዴ
የበረደው ጎኔ ይሞቀው ጀመረ
እስከመጨረሻው እድሌ ባማረ
መቼም እድሜ ያረዝማል የሰው መልካም ምኞት የሰው ምርቃት
ትሁንልህ በሉኝ ነፍሷን ከነብሴ ጋር አብሮ እንዲያዘልቃት
ይቻት ይቻት ይቻት ይቻት
በአይኗ ተመልክታኝ ባይኔ ተመልክቻት አዬ ድርሻዬ አይቻት
አፈቀርኳት እንጂ መች ቀረሁኝ ትቻት
ታድሏል አካሌ ይዟል ድርሻውን
ታድሏል አካሌ ይዟል ድርሻውን
ብቻ ያዝልቅልን መጨረሻውን
ታድሏል አካሌ ይዟል ድርሻውን
ታድሏል አካሌ ይዟል ድርሻውን
ብቻ ያዝለቅልን መጨረሻውን
ብንገናኝ አንድ ቀን ተዋውቀን
ይኸው አለን ተደስተን ስቀን
አሁን ነው የገባኝ በፍቅር ማለቄ
ታምና ስትጠጋኝ እች ሰው ማዕረጌ
እንደጎበዝ ኒሻን ደምቃ ባትዋብም በብዙ ቀለማት
ትዋል ከደረቴ ያካላቴ ጌጥ ነች የልቤ ሽልማት
ከዳር ስጠብቀው የፍቅሬን መድረሻ
ከመሀል ተገኘች የኔ መጨረሻ
መጠኔን ስፈልግ ልቤን በየአቅጣጫው
በዚም በዚያም ልኬ
አሻግሬ ሳያት ከወዲያ ሳስባት
በዚህ መጣች ልኬ
ይቻት ይቻት ይቻት ይቻት
በአይኗ ተመልክታኝ ባይኔ ተመልክቻት አዬ ድርሻዬ አይቻት
አፈቀርኳት እንጂ መች ቀረሁኝ ትቻት

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists