Tamrat Desta - Shegnugn lyrics
Artist:
Tamrat Desta
album: Kanchi Aybeltem
ሸኙኝ ልሂድ በቃ ይዘጋጅልኝ ሻንጣዬ
ምን ቀረኝ ሳልነግራት መጥቼ ሳጣት እሷን ብዬ
ያው እኔማ የመጣሁት ሁሉን ጥዬ
ከሠው ሀገር እዚ ድረስ እሷን ብዬ
ምን ሠራለሁ ምን ሠራለሁ
የሰው ሆኖ ከቆየኝ ፍቅሬ
እዛዉ ልሂድ እዛዉ ልሂድ
እሷን ብሎ በመጣው እግሬ
ያው እኔማ የመጣሁት ሁሉን ጥዬ
ከሠው ሀገር እዚ ድረስ እሷን ብዬ
ምን ሠራለሁ ምን ሠራለሁ
የሰው ሆኖ ከቆየኝ ፍቅሬ
እዛዉ ልሂድ እዛዉ ልሂድ
እሷን ብሎ በመጣው እግሬ
♪
እኔ እዚ ስመጣ በናፍቆት ትዝታ ተንገብግቤ
ውስጤ መች ገመተ የሌላ መሆንዋን መች አስቤ
ስትሄድ ያስቀመጠከው የፍቅር ውጥን ግራ ቀኙ
በቃ የሰው ሆናል በል አርፈህ ተቀመጥ ልቤ ሞኙ
በል እስኪ አርፈህ ተቀመጥ ገራገር ሰውን አማኙ
ሚስኪኑ የዋሁ ልቤ በፍቅር ሁልጊዜ ሞኙ
ፈጣሪ ይሁን ካላላው አብሮነት እሱ ካልፃፈው
አይሠምርም ሠው እህል ውሀ በግሉ ቢጥር ቢያግደው
አይሠምርም ሠው እህል ውሀ በግሉ ቢጥር ቢያግደው
♪
ያው እኔማ የመጣሁት ሁሉን ጥዬ
ከሠው ሀገር እዚ ድረስ እሷን ብዬ
ምን ሠራለሁ ምን ሠራለሁ
የሰው ሆኖ ከቆየኝ ፍቅሬ
እዛዉ ልሂድ እዛዉ ልሂድ
እሷን ብሎ በመጣው እግሬ
♪
የስራዋን ስጣት አልልም አትየው መበደሌን
ብረግም እራሴን ነው ለዚ ያበቃነኝን ክፋ እድሌን
ጠብቃ ጠብቃ ዛሬ የሠው ብትሆን ቢሞት ህልሜ
እሷም እውነት አላት ሳያቁት ይሄዳል የሠው እድሜ
ለጊዜው ቢጎዳ ውስጤ ክፋ ነሽ እኔ አልላትም
ብትወስን እውነቱ አላት ልክ ናት በሷም አልፈርም
እኔ ግን ምንም አልሠራም ልመለስ እዛው በርሬ
ለፍቅር እሷን ፍለጋ ገስግሶ በመጣው እግሬ
ለፍቅር እሷን ፍለጋ ገስግሶ በመጣው እግሬ
ገስግሶ በመጣው እግሬ
ገስግሶ በመጣው እግሬ
ገስግሶ በመጣው እግሬ
ገስግሶ በመጣው እግሬ
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist