Kishore Kumar Hits

Tamrat Desta - Tizita lyrics

Artist: Tamrat Desta

album: Kanchi Aybeltem


እህህ የኔ አለም የኔ አመል አንድ ነው አሂሂ
እህህ የኔ አለም ከአንድ ያላምደኛል
እህህ የኔ አለም መለየት አልወድም አሂሂ
እህህ የኔ አለም ጤና ይነሳኛል
አንችው ጋር ይቀመጥ የልቤ ትርታ
አስጨነቀኝ እዚህ ደጋግሞ እየመጣ
አንችው ጋር ይቀመጥ የልቤ ትርታ
አስጨነቀኝ እዚህ ደጋግሞ እየመጣ
የደጃፌን መዝጊያ
ክፍት አድርጌው ነበር
ዛሬም አልተዘጋ
ሳትመለስ ስትቀር
አይኔ በእንባ ጭጋግ
እንደተጋረደ
ስንት ፀደይ ጠብቶ
ስንት ክረምት ሄደ
እየቆረቆረኝ ያሰረኝ ከእግር እስከ ራሴ
አጎዛው ሊጥለኝ ሲታገለኝ ተረበሸች ነብሴ
አንችው ጋር ይቀመጥ እባክሽን የፍቅሬ ትዝታ
የማትመጪ እንደሆን የማትመጪ እኔ ለምን ልንገላታ
የማትመጪ እንደሆን የማላይሽ
ለክፉ አትምጪ ትዝታ
ምነው ቢተወኝ ባይቀሰቅሰኝ
በሌለሽበት ባይመጣ
የማትመጪ እንደሆን የማላይሽ
ለክፉ አትምጪ ትዝታ
ምነው ቢተወኝ ባይቀሰቅሰኝ
በሌለሽበት ባይመጣ

እህህ የኔ አለም የኔ አመል አንድ ነው አሂሂ
እህህ የኔ አለም ከአንድ ያላምደኛል
እህህ የኔ አለም መለየት አልወድም አሂሂ
እህህ የኔ አለም ጤና ይነሳኛል
አንችው ጋር ይቀመጥ የልቤ ትርታ
አስጨነቀኝ እዚህ ደጋግሞ እየመጣ
አንችው ጋር ይቀመጥ የልቤ ትርታ
አስጨነቀኝ እዚህ ደጋግሞ እየመጣ
የማትመጪ እንደሆን
የማንተያይ
ልቤን መልሺልኝ
ሌላ ሰው እንዳይ
ትዝታን የሚያስር
አዋቂ ቢገኝ
ደጅ ለመጥናቱ
ሰው ባልቀደመኝ
እየቆረቆረኝ ያሰረኝ ከእግር እስከ ራሴ
አጎዛው ሊጥለኝ ሲታገለኝ ተረበሸች ነብሴ
አንችው ጋር ይቀመጥ እባክሽን የፍቅሬ ትዝታ
የማትመጪ እንደሆን የማትመጪ እኔ ለምን ልንገላታ
የማትመጪ እንደሆን የማላይሽ
ለክፉ አትምጪ ትዝታ
ምነው ቢተወኝ ባይቀሰቅሰኝ
በሌለሽበት ባይመጣ
የማትመጪ እንደሆን የማላይሽ
ለክፉ አትምጪ ትዝታ
ምነው ቢተወኝ ባይቀሰቅሰኝ
በሌለሽበት ባይመጣ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists