Kishore Kumar Hits

Tamrat Desta - Selina (Ethiopian Eritrean Contemporary) lyrics

Artist: Tamrat Desta

album: Selina (Ethiopian Eritrean Contemporary)


ሠሊናዬ ሠሊናዬ አንቺን ማሠብ ሆኗል ትዝታዬ
ሠሊናዬ ሠሊናዬ ጓል ሀገረይ ፍቅረይ መአዛዬ
ለጤናሽ ደናነሽ ወይ ሠላም ነሽ ወይ ፍቅሬ አለሽ ወይ
በፍቅር ያሳለፍነው ጣፋጭ ጊዜ ይረሳል ወይ
ነይ ፍቅረይ ፍቅረይ ሠሊናዬ ሠሊናዬ
ድምፅሽን እስኪ አሠሚኝ አለው በይኝ
ነይ ፍቅረይ በሀገረይ አብሮ አደጌ የመጀመሪያዬ ትዝታዬ
ኦ ፍቅረይ በይነይ ሠሊናዬ በጃክምሮ
ደሀበስቀምኒ ካብ ፅማዶ
ምእባ ሠሊናመ በሀቢተይ
አይ ክብርነ ምግባር ንገዝተ

አድማስን አልፎ በመንፈስ ይድረስሽ የልቤ ሠላምታ
የተዋደደ መገናኘቱ አይቀር ምንም ቢርቁት
ሳስብሽ አለው ያልተቋጨ ፍቅር ናፍቆት ተሸክሜ
አንቺን አጥቼ አይመስለኝም ነበር ችዬ ምሄድ ቆሜ
ትዝታዬ ነሽ የልብ ፍቅሬ
የታነፅኩብሽ ሁሉ ነገሬ
በይ የሀገሬ ልጅ የማለዳዬ
እጠብቅሻለው ከነ አደራዬ
ለጤናሽ ደናነሽ ወይ ሠላም ነሽ ወይ
ፍቅሬ ሆይ ከኔ ርቀሽ አስቻለሽ ወይ
ለጤናሽ ደናነሽ ወይ ሠላም ነሽ ወይ
ፍቅሬ ሆይ ከኔ ርቀሽ አስቻለሽ ወይ

ነይ ፍቅረይ በይ ነይ ሠሊናዬ ሠሊናዬ
ድምፅሽን እስኪ አሠሚኝ አለው በይኝ
ነይ ፍቅረይ በሀገረይ አብሮ አደጌ
የመጀመሪያዬ ትዝታዬ
አብሮ ማደጉ የልጅነት ሳቁ ጨዋታውም ቀረ
እንዴት ይከብዳል ሠው ድንገት ሲለያይ እየተፋበረ
እስከመቼ ነው ላይሽ እየጓጓው የማለፋው አይኔን
አረ አለው በይኝ ድምፅሽን ልስማው ብሩህ ይሁን ቀኔ
አብረን ተምረን አብረን አድገን
መለያየቱን መች አስበን
ክፉ ቀን መጥቶ እንደለየን
ደግ ቀን ደግሞ ያገናኘን
ለጤናሽ ደናነሽ ወይ ሠላም ነሽ ወይ
ፍቅሬ ወይ ከኔ ርቀሽ አስቻለሽ ወይ
ለጤናሽ ደናነሽ ወይ ሠላም ነሽ ወይ
ፍቅሬ ወይ ከኔ ርቀሽ አስቻለሽ ወይ
ሠሊና ሠሊና
አይትመአለሊ አንቾቲ ሠሊና
አበይ መሀድኩ ብንሀበቢና
ህዝብ ለየ ፅባ ፀአለ ገደሎ
ብርመ ፍቅር ነይ ብርሀን ይላሎ
አይሻለው ደግሞ አምናለው አንድ ቀን
እንደ ዋዛ አንቀርም እንዲ ተራርቀን
የአጋጣሚ ጉዳይ ጊዜ ቢለያየን
ፍቅር ተስፋ ካለ እንገናኛለን
ሠሊና ሠሊና
አይትመአለሊ አንቾቲ ሠሊና
አበይ መሀድኩ ብንሀበቢና
ህዝብ ለየ ፅባ ፀአለ ገደሎ
ብርመ ፍቅር ነይ ብርሀን ይላሎ
አይሻለው ደግሞ አምናለው አንድ ቀን
እንደ ዋዛ አንቀርም እንዲ ተራርቀን

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists