Kishore Kumar Hits

Tamrat Desta - Mamayie lyrics

Artist: Tamrat Desta

album: Keza Sefer


የዘጠኝ ወር ብቻ አይደለም
የእኔ እና ያንቺ ነገር
አያልቅም ቢነገር
ሰላምሽን አብዝቶልኝ
ጤናውን ሰቶሽ
ሁሌም ያኑርሽ እማማዬ
ሚስጥር ገበናዬ ዎዎዎ ማማዬ
የእናት ጓደኛዬ ማማዬ
ሚስጥር ገበናዬ ማማዬ
የእናት ጓደኛዬ

ሺ አጀብ ቢበዛ ቢከበኝ ወዳጅ ዘመድ
ምድርን ባካልላት የት ብደርስ የትስ ብሄድ
ቢሞላኝ ሀብት እና ንዋይ
ታምራት ቢሆንም ደስታ
ለኔ ግን የዚህ አለም ነገር
አይተካም አንቺ እናቴን
አይተካም አንቺ እናቴን
ኤኤኤ ኤኤኤ
ወዳጅ ቢሉሽ ወዳጅ (ወዳጅ)
ከወዳጅ በላይ ነሽ
እህት ቢሉሽ ወንድም (ወንድም)
ሁሉን ታስንቂያለሽ
ማማዬ (ማማ) ማማዬ (ማማ)
ማማዬ (ማማ) ማማዬ (ማማ)
እናቴ (ማማ) እምዬ (ማማ)
ማማዬ (ማማ) ማማዬ (ማማ)
ማማዬ (ማማ) ሚስጥር ገበናዬ

የዘጠኝ ወር ብቻ አይደለም
የእኔ እና ያንቺ ነገር
አያልቅም ቢነገር
ሰላምሽን አብዝቶልኝ
ጤናውን ሰቶሽ
ሁሌም ያኑርሽ ማማዬ
ሚስጥር ገበናዬ ዎዎዎ ማማዬ
የእናት ጓደኛዬ ማማዬ
ሚስጥር ገበናዬ ማማዬ
ማማዬ የእናት ጓደኛዬ

አንሼ እንዳልታይ (ሳይኖርሽ እንዳኖርሽኝ)
እቅፍ ድግፍ አርገሽ (በፍቅርሽ እያቆምሽኝ)
ደስተኛ ሆኜ እንድኖር
ባንቺ ውስጥ እራሴን እያየው
ጠዋት ማታ ሁሌም በጸሎት
አምላኬን እማጸናለው
ፈጣሪን እማጸናለው
ኤኤኤ ኤኤኤ
ወዳጅ ቢሉሽ ወዳጅ (ወዳጅ)
ከወዳጅ በላይ ነሽ
እህት ቢሉሽ ወንድም (ወንድም)
ሁሉን ታስንቂያለሽ
ማማዬ (ማማ) ማማዬ (ማማ)
ማማዬ (ማማ) ማማዬ (ማማ)
እናቴ (ማማ) እምዬ (ማማ)
ማማዬ (ማማ) ማማዬ (ማማ)
ማማዬ (ማማ) ሚስጥር ገበናዬ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists