Tamrat Desta - Yeken Tsedal lyrics
Artist:
Tamrat Desta
album: Keza Sefer
የተቸረሽ ድንቅ ተአምር
ዉስጥሽ ላዩም ቢዋብ ቢያምር
አይደለሽም እህደ ጥበብ
ሰራሽ እንጂ የአምላክ ሀሳብ
የተቸረሽ ድንቅ ተአምር
ዉስጥሽ ላዩም ቢዋብ ቢያምር
አይደለሽም እህደ ጥበብ
ሰራሽ እንጂ የአምላክ ሀሳብ
ደመናን ፈትሎ ሸማኔ ሳይሰማ
ለአንቺ አልብሶሻል የዉበትን ሸማ
የእጆቹን ስራ የጥበበቡን ሚስጥር
በአንቺ ላይ ታይቷል ዉበት እና ፍቅር
እንደ ዉቅያኖስ ጥልቅ አርጎት
ከተኔ አርቅቆት
አንድ አንቺን ሰራሽ ፈጣሪ
አቤት ስታምሪ
እንደ ዉቅያኖስ ጥልቅ አርጎት
ከተኔ አርቅቆት
ዉብ አርጎሽ ሰራሽ ፈጣሪ
አቤት ስታምሪ
የቀን ፀዳል አድርጎሻል
እንደ ፀኃይ አብርተሻል
የሚቆጨኝ አንድ ነገር
የሀገሬ ልጅ ባትሆኝ ነበር
የተቸረሽ ድንቅ ተአምር
ዉስጥሽ ላዩም ቢዋብ ቢያምር
አይደለሽም እህደ ጥበብ
ሰራሽ እንጂ የአምላክ ሀሳብ
ካማረዉ ስፍራ ምድር ተፈጥረሽ
ምን አለ በአንቺ የማያምርብሽ
የሰዉ መዉደድን ፍቅር አድሎሽ
የአዳም ዘር ሁሉ ተገረመብሽ
እንደ ዉቅያኖስ ጥልቅ አርጎት
ከተኔ አርቅቆት
አንድ አንቺን ሰራሽ ፈጣሪ
አቤት ስታምሪ
እንደ ዉቅያኖስ ጥልቅ አርጎት
ከተኔ አርቅቆት
ዉብ አርጎሽ ሰራሽ ፈጣሪ
አቤት ስታምሪ
የቀን ፀዳል አድርጎሻል
እንደ ፀኃይ አብርተሻል
የሚቆጨኝ አንድ ነገር
የሀገሬ ልጅ ሳትሆኝ ነበር
Поcмотреть все песни артиста
Other albums by the artist