Kishore Kumar Hits

Tilahun Gessesse - Lenat Ethiopia lyrics

Artist: Tilahun Gessesse

album: Hulume Behager New


ኢትዮጵያ 3x የእኛ መመኪያ
ኢትዮጵያ 3x የእኛ መመኪያ
እናት ሀገር እትዮጵያን 2x
ኢትዮጵያ የእኛ መመኪያ
የሰው ዘር ትስስር
ልዑል ሐብት መቁጠሪያ 2x
የነፃነት ምኩራብ የታሪክ መስፈሪያ
የእግዚአብሔርን ብሩክ ምድር ቅድስት ኢትዮጵያ
የጥቁር ህዝብ ክብር
የማዕዘን ድንጋይ 2x
የተጋድሎ አፅ መርህ
የደም ፍሳሸ ብቃይ
የምድር ፍቅር ብስራት
የመስዋዕት ሜዳ
አ... ሀ...
የባህል ቅርስ ቋንቋ ሰገነት
አ... ሀ...
ኢትዮጵያ ሀገረ ገነት
አ... ሀ...
የባህል ቅርስ ቋንቋ ሰገነት
አ... ሀ...
ኢትዮጵያ ሀገረ ገነት
እናት ሀገር ኢትዮጵያ 2x
ኢትዮጵያ የእኛ መመኪያ
ኢትዮጵያ 3x የእኛ መመኪያ
ኢትዮጵያ 3x የእኛ መመኪያ
እናት ሀገር እትዮጵያን 2x
ኢትዮጵያ የእኛ መመኪያ
የጥቁር ዘር አርማ
ሰንደቅሽን ያመነ 2x
ህብረት ያደመቀው በእምነት የጀገነ
በቃል ሰንሰል እድመት ዜጋሽ የገነነ
የአንድነት የአክብሮት
የአትንኩኝ ባይነት 2x
የፅድቅ ቋሚ መዝገብ ምንጭ ነሽ አብነት
ኢትዮጵያ እናት ሀገር ኢትዮጵያ ነሽ እውነት
አ... ሀ...
በነፃነት በአንድነት ፈርጅሽ
አ... ሀ...
ጠላትሽም ይወድቃል ከጅሽ
አ... ሀ...
በነፃነት በአንድነት ፈርጅሽ
አ... ሀ...
ጠላትሽም ይወድቃል ከጅሽ
እናት ሀገር ኢትዮጵያ 2x
ኢትዮጵያ የእኛ መመኪያ 3x

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists