Kishore Kumar Hits

Tsehaye Yohannes - Blen lyrics

Artist: Tsehaye Yohannes

album: Sakilgne


ምስቅልቅል ሕይወቴ ሕይወቴ
በፍቅርሽ አማረ
የስኬቴ መንገድ ጎዳና
ባንቺ ተጀመረ
አነሳሁሽ በደግ በደግ
ጸሎቴን ለአምላኬ ሳደርግ
አነሳሁሽ በደግ በደግ
ጸሎቴን ለአምላኬ ሳደርግ
የጥሩ አፍቃሪ ናሙና
የውስጤም ብርታት ነሽና
አነሳሁሽ ጸሎቴን ለአምላኬ ሳደርግ
ሕይወቴ ሠምሮ እንዲቃና
ከእኔ እኩል ለፍተሻልና
አነሳሁሽ ጸሎቴን ለአምላኬ ሳደርግ
ተመስገን ስለው ጠዋት ማታ
አልረሳም ያንቺን ውለታ
አነሳሁሽ ጸሎቴን ለአምላኬ ሳደርግ
በሕይወቴ ዘመን በደስታ በኀዘኔ
ሁሉን ያየሁብሽ ብሌኔ ነሽ የዓይኔ
በሕይወቴ ዘመን በደስታ በኀዘኔ
ሁሉን ያየሁብሽ ብሌኔ ነሽ የዓይኔ
ብሌኔ ብሌኔ
የማይሽ እንደ ዓይኔ
ብሌኔ ብሌኔ
ብርሃኔ ነሽ ለኔ
ብሌኔ ብሌኔ
የማይሽ እንደ ዓይኔ
ብሌኔ ብሌኔ
ብርሃኔ ነሽ ለኔ
ምስቅልቅል ሕይወቴ ሕይወቴ
በፍቅርሽ አማረ
የስኬቴ መንገድ ጎዳና
ባንቺ ተጀመረ
አነሳሁሽ በደግ በደግ
ጸሎቴን ለአምላኬ ሳደርግ
አነሳሁሽ በደግ በደግ
ጸሎቴን ለአምላኬ ሳደርግ
በፍቅርሽ ዓይኔን ገለጥኩኝ
በቃ አሁን መኖር ጀመርኩኝ
አነሳሁሽ ጸሎቴን ለአምላኬ ሳደርግ
ሰው ሆነሽ ሰው አደረግሺኝ
ዓይኔንም በዓይኔ አሳየሺኝ
አነሳሁሽ ጸሎቴን ለአምላኬ ሳደርግ
ኑሮዬን እየተጋራሽ
በውስጤ ሰላም የዘራሽ
አነሳሁሽ ጸሎቴን ለአምላኬ ሳደርግ
በሕይወቴ ዘመን በደስታ በኀዘኔ
ሁሉን ያየሁብሽ ብሌኔ ነሽ የዓይኔ
በሕይወቴ ዘመን በደስታ በኀዘኔ
ሁሉን ያየሁብሽ ብሌኔ ነሽ የዓይኔ
ብሌኔ ብሌኔ
የማይሽ እንደ ዓይኔ
ብሌኔ ብሌኔ
ብርሃኔ ነሽ ለኔ
ብሌኔ ብሌኔ
የማይሽ እንደ ዓይኔ
ብሌኔ ብሌኔ
ብርሃኔ ነሽ ለኔ
ብሌኔ ብሌኔ
የማይሽ እንደ ዓይኔ
ብሌኔ ብሌኔ
ብርሃኔ ነሽ ለኔ
ብሌኔ ብሌኔ
የማይሽ እንደ ዓይኔ
ብሌኔ ብሌኔ
ብርሃኔ ነሽ ለኔ
ብሌኔ ብሌኔ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists