Kishore Kumar Hits

Tsehaye Yohannes - Ande Beygne lyrics

Artist: Tsehaye Yohannes

album: Sakilgne


ፍቅርሽ እንደጥላ እንደጥላ ሲቀርቡት ይርቃል
ደሞ ቁርጥ አርገዉ ሲተዉት ዞሮ ይናፍቃል
ዛሬ አገኘሁሽ ስል ሲነጋ የለሽም ከጐኔ
ላም አለኝ በሰማይ ሆነብኝ ያንቺስ ፍቅር ለኔ
እንደዉ የአንቺን ነገር ሳስበዉ አንዳንዴ ግራ ይገባኛል
ግርም ይለኛል ድንግር ይለኛል
የማደርገዉ ሳጣ ትቅርብኝ እልና ልቤ አልቆርጥ ይለኛል
አልቆርጥ ይለኛል አልቆርጥ ይለኛል
አንድ ሰሞን መተሸ ተስፋ እየመገብሽኝ አለዉ ትይኝና
አለዉ ትይና ታጓጉኚና
ደሞ ለአንድ ሰሞን ታስጨንቂኛለሽ ጠፍተሸ እንደገና
ደሞ እንደገና ደሞ እንደገና
አንድ በይኝ መላ አንድ በይኝ አንድ በይኝ መላ
ስከተልሽ ምን ያርቅሻል እንደ ምሸት ጥላ
አንድ በይኝ መላ አንድ በይኝ አንድ በይኝ መላ
ስከተልሽ ምን ያርቅሻል እንደ ምሸት ጥላ
ፍቅርሽ እንደጥላ እንደጥላ ሲቀርቡት ይርቃል
ደሞ ቁርጥ አርገዉ ሲተዉት ዞሮ ይናፍቃል
ዛሬ አገኘሁሽ ስል ሲነጋ የለሽም ከጐኔ
ላም አለኝ በሰማይ ሆነብኝ ያንቺስ ፍቅር ለኔ
በቃ ሄደች ብዬ ቀን አንቺን ለመርሳት ሳስብ ሳመነታ
ቀን ሳመነታ ቀን ሳመነታ
ባላሰብኩት ሰዓት ምነዉ ጠፋህ ብለሽ ትመጫለሽ ማታ
የማታ ማታ የማታ ማታ
ተወደድኩኝ ብለሽ ከሆነም ነግረሽኝ ባዉቀዉ ይሻለኛል
ባቅ ይሻለኛል ባዉቅ ይሻለኛል
ፍቅርሽ ሲያስመርረኝ ምን አልባት አንድ ቀን ሆድ ይቆርጥልኛል
ይቆርጥልኛል ይቆርጥልኛል
አንድ በይኝ መላ አንድ በይኝ አንድ በይኝ መላ
ስከተልሽ ምን ያርቅሻል እንደ ምሸት ጥላ
አንድ በይኝ መላ አንድ በይኝ አንድ በይኝ መላ
ስከተልሽ ምን ያርቅሻል እንደ ምሸት ጥላ
ፍቅር ዕዳ ነዉ ምን ዕዳ ነዉ ፍቅር ዕዳ ነዉ ምን ዕዳ
ምን ዕዳ ነዉ ፍቅርስ ዕዳ አንዱ ብቻ ሲጐዳ
ፍቅር ዕዳ ነዉ ምን ዕዳ ነዉ ፍቅር ዕዳ ነዉ ምን ዕዳ
ምን ዕዳ ነዉ ፍቅርስ ዕዳ አንዱ ብቻ ሲጐዳ
አንድ በይኝ መላ አንድ በይኝ አንድ በይኝ መላ
ስከተልሽ ምን ያርቅሻል እንደ ምሸት ጥላ
አንድ በይኝ መላ አንድ በይኝ አንድ በይኝ መላ
ስከተልሽ ምን ያርቅሻል እንደ ምሸት ጥላ
ፍቅር ዕዳ ነዉ ምን ዕዳ ነዉ ፍቅር ዕዳ ነዉ ምን ዕዳ
ምን ዕዳ ነዉ ፍቅርስ ዕዳ አንዱ ብቻ ሲጐዳ
ፍቅር ዕዳ ነዉ ምን ዕዳ ነዉ ፍቅር ዕዳ ነዉ ምን ዕዳ
ምን ዕዳ ነዉ ፍቅርስ ዕዳ አንዱ ብቻ ሲጐዳ

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists