Kishore Kumar Hits

Tsehaye Yohannes - Yewahlibe lyrics

Artist: Tsehaye Yohannes

album: Sakilgne


የዋህ ልቤ እንጊዲህ ቅመሰዉ
ለምን አመንክ የማይታመን ሰዉ
ስትከተላት በልጣብህ ከኔ
ይህ ይመጣል መች አልክ ያኔ
የዋህ ልቤ እንጊዲህ ቅመሰዉ
ለምን አመንክ የማይታመን ሰዉ
ስትከተላት በልጣብህ ከኔ
ይህ ይመጣል መች አልክ ያኔ
ይገርመኛል እኔ የአንተ ማንገራገር
ጊዜህ ሲጠፋ ባበቃ ነገር
ወይ አላወክበት ሰዶ ማሳደዱን
ከራስህ ጥፋት የመጣዉን ጦስ በል ቻለዉ መንገዱን
ምነዉ በቀደምካት ያን ጊዜ ሳትቀድምህ
ሰላም ሳታጣ እንዲህ ሳያምህ
የእሷን ሳትቀበል የአንተን ማን ስጥ አለህ
እንደ ጥፋትህ ቅጣትህ ቀሏል ልቤ እድለኛ ነህ
እንጊዲህ ልቤ አደብ ግዛ
ጭንቀት ሀዘን አንግዛ
ያ ፍቅሯን ላታገኝ
የማይሆን ስትመኝ
እሷን እሷን ስትል ርቀኸኝ ሳታቆም
የዋህ ልቤ እንጊዲህ ቅመሰዉ
ለምን አመንክ የማይታመን ሰዉ
ስትከተላት በልጣብህ ከኔ
ይህ ይመጣል መች አልክ ያኔ
ከጅምሩ ነበር እሳትን በቅጠል
ዉስጥ ዉስጡን ነዶ ሳይቀጣጠል
የወደደ እራሱን ይጐዳል ቢባልም
ልቤ የአንተ ግን ራስን መጣል ነዉ ፍቅር አይባልም
የትርታዬ ዋስ ልቤ ዋስትናህ
ዘመድህ እኔ ሰላም ጤናህ
ለምን አተዋትም እንደሷ ወስነህ
ያለፈን ስትል ጊዜ ቢያልፍብህ ተጐጂዉ አንተ ነህ
እንጊዲህ ልቤ አደብ ግዛ
ጭንቀት ሀዘን አንግዛ
ያ ፍቅሯን ላታገኝ
የማይሆን ስትመኝ
እሷን እሷን ስትል ርቀኸኝ ሳታቆም
እንጊዲህ ልቤ አደብ ግዛ
ጭንቀት ሀዘን አንግዛ
ያ ፍቅሯን ላታገኝ
የማይሆን ስትመኝ
እሷን እሷን ስትል ርቀኸኝ ሳታቆም

Поcмотреть все песни артиста

Other albums by the artist

Similar artists